Blog > Employers

የድርጅታችሁን ባህል ጠብቆ ለማቆየት እና ስራችሁ ለማሻሻል የሚጠቅሙ 7 ባህሪያት

አብዛኞቹ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የድርጅታቸውን ባህል የማሳደግ ድክመት ይስተዋልባቸዋል፡፡ በተለይ በአሁን ጊዜ አጥጋቢ ባልሆነው የደንበኛ እና የሠራተኛ ፍሰት ተወዳዳሪ ሆኖ መቆየት ከባድ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ ህዝቦች ከደንበኞች ጋር ቅርበት እንዲፈጥሩ ማድረግ፣ ገበያውን ማጥናት እና ውሳኔ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡

አንድ መፅሀፍ ላይ የሰፈረው መግለጫ ምን ይላል፤ ስኬታማ ድርጅቶች ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት የደንበኞቻቸውን ስሜት በማዳመጥ፣ የዝንባሌን ባህል የማዳበር ግንባታ እና አስተዳደር ላይ ሲሆን ቡድናቸው ውሳኔዎችን መወሰን እንዲችሉ እና አዲስ ምርቶች በቋሚነት ማምረት እንዲችሉ ማድረግ ነው፡፡ 7 መደገፍ ያለብን የባህል ባህሪያት እንመልከት፡-   

1. ሁሉንም መልሶች እንደማታውቁ መቀበል

ዛሬ እናንተ እና ቡድናችሁ የምታውቁት የገበያ ሁኔታ ነገ ሊቀየር ይችላል፡፡ መልሶችን ባፋጣኝ እና በእርግጠኛነት መውሰድ እና መገመት ተገቢ አይደለም፡፡ ከደንበኛ ጋር ሚ የሆነ ውይይት ማካሄድ፣ ሙከራዎችን ማድረግ እና አስፈላጊ የሆነውን ምሰሶ ማቆም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቆየት ተመራጭ ነው፡፡

 

2. ቡድናችሁ ውድቀትን እንዲያስተናግድ መፍቀድ

መከራዎች የትምህርት ውጤቶች ናቸው ግን ተፈጥሮአዊ ሙከራ በተደጋጋሚ ውድቀትን ያስተናግዳል፡፡ ውድቀት ሲታወቅ፤ ቡድኑ ስጋቶችን ይቀበላል ስራችሁም ይሻሻላል፡፡ ወቀሳ የሌለበትን ስራ መልመድ ምን ጥሩ ተሰራ ምን መረጥ አለበት የሚለውን ለማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

 

3. የራስ መመሪያን ማሳደግ

ተልእኮዋችሁ ግልፅ ሲሆን እና ድርጅቱ በግልፅ ሲያስቀምጠው የራስ መመሪያችሁን መሰረት እና መፍትሄዎቹን ማግኘት ይቻላል፡፡ የቡድን አባላቶች ለጥራት፣ ለፈጠራ፣ ለትብብር እና ለትምህርት የግል ሀላፊነትን መውሰድ ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ አካባቢያችሁን ማዘጋጀት እና ለስኬት ማበረታታት አስፈላጊ ነው፡፡

 

4. ሀቀኝነትን ማዳበር

በፍፁም መልክተኛ አትላኩ፤ ማለት ያለባቸውን ባትወዱትም መልስ ከመስጠታችሁ በፊት ሁሉንም በጥሞና ማዳመጥ እንዳለባችሁ አትርሱ፡፡ መጠነኛ በሆነ ስሜት ጥያዌዎችን ጠይቁ፣ ሁልጊዜም አዎንታዊ እና የሚቻሉ መፍትሄዎች ላይ አተኩሩ፡፡ ማንም ሰው የሚማረው ግንኙነትን እና ስህተትን ከማጣት አይደለም፡፡  

 

5. ለወደፊት እርምጃ አድሎን መለማመድ

መደበኛ ክርክር ማድረግ እና እንደገና መተንተን በፍጥነት ለመÕዝ እና የገበያ ቦታዎችን ለመወዳደር አስቸጋሪ ነው፡፡ አሁን ያለው የስኬት ሂደት ባህል ግምት ግን ማንኛውንም ትንንሽ ውሳኔዎች፣ መልሶ የመቀበል ፍላጎት እና የምዘና ማስረጃ ሁልጊዜም ወደፊት እንደሚያስኬድ ነው፡፡

 

6. የደንበኞችን ዋጋ እንደ ብቸኛ የስራን አቅጣጫ ዋጋ መተመን

የደንበኞች እይታ በአሁን ጊዜ ጠንካራ ገበያን ለማስተዳደር አስፈላጊ ነው፡፡ ዋና ተወካዮች፤ ደንበኞች ለመስራት የሞከሩትን፣ በመንገዳቸው ምን እንዳለ እና እንዴት ልትረዱዋቸው እንደምትችሉ መረዳት አለባችሁ፡፡

 

7. የቡድን ባህል የሆነውን ትብብርን፣ የሀሳብ ልዩነትን እና እምነትን መገንባት

ጥሩ የሚባለው ቡድን ትንሽ የሀሳብ ልዩነት ያለው፣ በአጭር ጊዜ የሚሰራ እና የምልልስ ኡደት ያለው ነው፡፡ ረዥም ጊዜ የሌለው እና ልዩ በሆነ ስራ ላይ ቀጣይነቱን የሚያጎለብት ነው፡፡ አሁን ብዙ አይነት ምልከታ ያለው ሰው ያስፈልጋል ግን በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ባፋጣኝ መተባበር፣ አዎንታዊ ውጤቶችን መፍጠር እና እርስ በእርስ መተማመን ያስፈልጋል፡፡

 

ድርጅቶች በአሁን ጊዜ ከእነዚህ የባህል ባህሪያት ጋር በተሻሻለ መጠን ባንድአፍታ መልስ እያገኙ እና የሠራተኛ ባህሪም ብቅ እያለ ስኬታማ እየሆኑም ናቸው፡፡