Blog > Self Development

የተሻለ አክብሮትን ለማግኘት የሚረዱ 7 መንገዶች

የሀላፊነት ቦታ ላይ ስትሆኑ አብረዋችሁ ከሚሰሩት ሠዎች አክብሮት ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

አክብሮት ስጦታ አይደለም፤ምንግዜም የሠው ልጅ መከበርን ይፈልጋል፡፡ የስራ ባልደረቦቻችሁ በስራ ገበታ ላይ የማክበር ልምድ ይኖራቸው ይሆናል የእናንተም መረጃ ወይም ችሎታ ስራውን ለማስፈጸም ይጠቅማል ከዚህም ባለፈ መልኩ ግን አክብሮት ያስፈልጋል፡፡

ከሠዎች አክብሮትን ማግኘት ከቻላቹ በቀላል መንገድ ስኬታማ መሆን ትችላላችሁ! ይህንንም አክብሮት ለማግኘት የሚረዳ መላ እናካፍላችሁ፡፡

  1. መልካም ሁኑ

በቀን ውስጥ ለምታገኙዋቸው ሠዎች መልካም ጸባይን አሳዩ፡፡ ከቤተሰቦቻችሁ ጀምራቹ እስከ ስራ ባልደረቦቻችሁ እና በመዝናኛ ቦታም ላይ ላሉ ሠዎች ጥሩ ጸባይ ይኑራችሁ፡፡

ለሠዎች መልካም መሆን ከመናገር በላይ ከባድ ነው በተለይ ጥሩ ቀን ሳታሳልፉ ስትቀሩ የሚኖራችሁን ጸባይ ይዛችሁ ሰዎች እንዲያከብሩዋችሁ የምትፈልጉ ከሆነ እነርሱም የእናንተን አክብሮት ይጠብቃሉና ጥንቃቄ አድርጉ፡፡ ለራሳችሁ ልታገኙት የምትፈልጉትን ክብር ለሠዎች ለግሱ መልካም ለመሆን የሚቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡ በቀላል ምሳሌ፤ ወንበር መሳብ እና በር መክፈትን ከትህትና እና ከምስጋና ጋር አቅርቡ፡፡

 

  1. አክብሮትን አሳዩ

ሠዎችን ያስደብራል ብላችሁ የምታስብዋቸውን ነገሮች በሙሉ ማስወገድ ይኖርባችኃል፡፡ ለምሳሌ፤አይንን ማጉረጥረጥ፣በስልካችሁ መጠመድ ወይም ደግሞ ስለሌሎች ሠዎች አብዝታችሁ ማውራት (ሀሜት) አሁን አብረዋችሁ ላሉት ሠዎች ብቻም ሳይሆን ወደፊት ለምታገኙዋቸው የህይወት ተሞክሮዎች መንገድ ይዘጉባችኃል፡፡ በምትኩ ግን አካባቢያችሁን በጥሞና ማዳመጥ እና ማስተዋል አለባችሁ፡፡ ሁሉም ሠው መሰማትን ይፈልጋል! ምንም እንኩዋን ሁልጊዜም በሀሳብ መግባባት ከባድ ቢሆንም ያሠው ለእናንተ እንዲሰጥ የምትፈልጉትን ክብር ለእርሱም ማሳየት አለባችሁ፡፡

  

  1. በጥሞና አዳምጡ

ማዳመጥ መቻል ትልቅ ስጦታ ነው፡፡ አንድ ሠው ምንግዜም ግላዊ አመለካከቱን እና ሀሳቡን ሊነግራችሁ ሲሞክር የፈለገውን ነገር አዳምጣችሁ መረዳት መቻል አለባችሁ፡፡ በአሁን ጊዜ በብዙዎቻችን መካከል የሚስተዋለው ንግግር በተመሳሳይ ሀሳብ ላይ አለመግባባትን ነው በንግግር ወቅት ግላዊ አስተያየትን ከመስጠት ይልቅ ንግግሩን ለሚያደርገው ሠው ጥያቄዎችን በየመሀሉ መጠየቅ ይበልጥ እንዲያወራላችሁ ያደርጋል፡፡ የማዳመጥ ችሎታን ባዳበራችሁ ቁጥር ለሚያወራው ሠው ተፈላጊነቱን ታረጋግጡለታላችሁ፡

 

  1. ጠቃሚ ሁኑ

በማንኘውም አጋጣሚ እንደያስፈላጊነቱ ሠዎችን ለመርዳት እና ስሜታቸውን ለማዳመጥ ፍቃደኛ ስትሆኑ አክብሮትን ታገኛላችሁ፡፡ በሂወታችሁ ውስጥ ያሳለፋችሁትን መጥፎም ሆነ በጎ ጎን ለሠዎች ትምህርት እንዲሆን አካፍሉዋቸው፡፡ ሠዎች እርዳታን ሳይጠይቁዋችሁ ሀላፊነትን የመውሰድ ልምድ ቢኖራችሁ መልካም ነው፡፡ እስኪ በቀን ውስጥ ስንት ጊዜ ጠቃሚ ሆናችኃል?

 

  1. ከስህተታችሁ ተማሩ

የሠው ልጅ በአጋጣሚዎች ካልሆነ በስተቀር የሚያደርጋቸው ማንኛውንም ድርጊቶች በምርጫ የተሞሉ ናቸው ስለዚህ አውቀን ለምናደርጋቸው ድርጊቶች ምንም አይነት ይቅርታ ማድረግ አይኖርም፡፡ መጀመሪያም ለምታደርጉዋቸው ድርጊቶች የባለቤትነት ስሜት ይሰማችሁ፤ ብታረፍዱ በእርግጠኝነት ጊዜያችሁን ባግባቡ መጠቀም ባለመቻላችሁ ነው፣ ስራችሁን ካልጨረሳችሁ ትኩረት ባለመስጠታችሁ እና አስፈላጊ ባልሆኑ ነገሮች በመጠመዳችሁ ነው ስለዚህ ስህተታችሁን ይዛችሁ ከመቀመጥ ለማረም ጥረት አድርጉ፡፡ ያለፈውንም ለመርሳት በመሞከርም የተሻለ ለማድረግ በቁርጠኝነት ተነሱ፡፡

  

  1. ቁጣን አስወግዱ

ቂምን እና ንዴትን መያዝ ራስን ከመጉዳት በቀር ምንም ጥቅም የለውም፡፡ ንዴታችሁን ጊዜያዊ አድርጉ ከዛም ነገሮችን ለማቃናት መሞከር ወይም ባለበት መተው፡፡ ያናደዳችሁ ነገር ማንሰላሰል ጥቅም አይኖረውም፡፡ ጭንቀት ለስጋት እና ለጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል ማንም ሠው ፍጹም አይደለም፤ የሠው ልጅ በየጊዜው ጥፋት ያጠፋል ግን ነገሮችን በመልካም እና በአዎንታዊ አመለካከት ለመቀየር ትኩረት በማድረግ ለራሳችሁም ሆነ ለሠዎች ደስታን ፍጠሩ፡፡ ይቅርታ አድርጉ ከዛም ርግፍ አድርጋችሁ ተው፡፡

 

  1. ለለውጥ ፍቃደኛ ሁኑ

እራስን ወደተሻለ ለመቀየር ፍቃደኛ አለመሆን የትም አያደርስም፡፡ የለውጥን ሂደት ጠንቅቃችሁ ማወቅ አለባችሁ እንደ ሠው ለማደግ ጣሩ፣ አዲስ ችሎታን ለማግኘት መሞከር፣ እንቅስቃሴ ማድረግ እና በተለይ እራስን መፈተን ተመራጭ ነው፡፡ ምንግዜም እራሳችሁን የተሻለ ሠው ለማድረግ ተጉዙ፡፡

    

በተለያዩ  የስራ መደቦች ያወጡ ማስታወቅያዎችን ለመመልከት www.jobs.et

ይጎብኙ