Blog > Self Development

የሌሎችን አመለካከት መረዳት መቻል ለስኬታማ መንገድ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

የሌሎችን አመለካከት መረዳት መቻል ለስኬታማ መንገድ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?


ስኬታማ ለመሆን የሰዎችን ችሎታ በዋናነት ማግኘት ይኖርብናነል፡፡ ከሠዎች ጋር ስኬታማ ግንኙነትን
ለመፍጠር የእነሱን እይታ መመልከት መቻል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡-


1ኛ የሌሎችን አመለካከት መቀበል ከራሳችን አመለካከት ባሻገር የሌሎችን ብቃት መጋራት ነው፡፡
2ኛ የሠዎችን አመለካከት መቀበል ርህራሄን እንድናገናዝብ እና ግንኙነትን እንድናጠነክር ይረዳናል፡፡

እነዚህ 2 ሀሳቦች ላይ ስናተኩር ከሠዎች ዘንድ የአክብሮት መስተጋብር፣ስኬት እና በአንድነት
ዋስትናን እናገኛለን፡፡
የሠዎችን አመለካከት ለመቀበል የሚረዱ ቀላል መንገዶችን እንመልከት፤


1. ስለሌሎች ማሰብ
በሌሎች ሠዎች ህይወት ውስጥ ስንገባ እራስወዳድ ካልሆንን በስተቀር ምን እንደሚስቡ ለማሰብ ተፈጥሮ ያስገድደናል፡፡በደመነፍስም ሆነ ከምንም ተነስተን ምን እነደሚያደርጉ፣ ምን እነደሚያዩ እና የሰውነት እነቅስቃሴአቸው ምንን እነደሚያመላክት እንታዘባለን፡፡ ይህም የሚያሳየው ባቅራቢያቸው ስንሆን ምን ያህል ምቾት እንደሚሰማን፣መስተጋብር ለመፍጠር እነድንወስን እና እንዴት የተሻለ ግንኙነት መፍጠር እንዳለብን ያግዘናል፡፡ አቅራቢያችን ካሉት ሰዎች ጋር ምቾት ከተሰማን የበለጠ እንድንቀርባቸው እድሎች ይፈጠራሉ፡፡ ለምሳሌ፤ እነርሱን ለማናገር ጥሩ ጊዜ ላይ መሆናቸውን፣ ነጻ ወይም በስራ የተወጠሩ መሆን አለመሆናቸውን በማገናዘብ ለግንኙነታችን ውጤታማ ነው ብለን የምናስበውን ውሳኔ እንድንወስን ያደርጋል፡፡እነዚህን መረጃዎች ከሌሎች ማወቅ ከቻልን ንግግር ለማድረግ ስንዱ እንድኖን ወይም ለንግግር ምቹ ጊዜን እንድንጠብቅ መድረግ እንችላለን፡፡

2. ስሜታዊ ደንብ እና ሀሳብ
አመለካከትን መቀበል ከሌሎች ሠዎች ጋር ችሎታን ወይም ስሜትን መጋራት ብቻ አይደለም
የኛንም ችሎታ ለራሳችን ስሜት ደንብ እንደማውጣትም ነው፡፡ ከሠዎች ጋር ውጤታማ ለመሆንምን አይነት ዘዴ መጠቀም እንደሚያስፈልገን በቀላሉ እንድንገነዘብ ያደርጋል ስለዚህ ወዲያው የራሳችንን ትኩረት በሠዎች ዘንድ ምን እየተካሄደ እንዳለ እንድናውቅ ይረዳናል፡፡ ወደ ሀሳብ ሲመጣ ዋናው ነገር በቀረቡት ሁኔታዎች ላይ ምን ማድረግ እንዳለብን እራሳችንን መጠየቃችን ሳይሆን መሞከራችን እና ሌሎች ሠዎች ምን ማድረግ እንደሚችሉ መረዳታችን ነው፡፡ የኛ ሀሳብ ትክክለኛ ከሆነ እና ስሜታዊ ደንባችን ጠንካራ ከሆነ በምናደርጋቸው ማንኛውም ነገሮች ላይ የበለጠ ስኬታማ እንሆናለን፡፡ የሠውን ጥልቅ ባህሪ ማግኘት፣ የጸባይን ኩነት ማወቅ መቻል፣ ግምትን እና የሰዎችን ሀሳብ መረዳት ምናልባት ከእኛ የተለየ ባህሪ እንድናውቅ ያደርጋል ይህም ስኬትን ለማሳደግ የሚገባውን ግላዊ ትስስር ይፈጥራል ምክንያቱም ሠዎች የመደመጥ ዋጋ እና የመረዳት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡


3. ሠዎችን በትክክል መረዳት(ማንበብ)
ስሜት የሠዎችን አመለካከት የምኖስድበት መመዘኛ መንገድ ነው፡፡ ሠዎችን በቀላሉ እንድንረዳም ያግዘናል፡፡ እኛም በተፈጥሮ የሠዎችን ባህሪ ምን እንደሚያስቡ፣ ምን ለማድረግ እንደፈለጉ እና እንዳቀዱ ለማወቅ እንጥራለን አእምሮአችንም ማህበራዊ ሁኔታዎችን ለማወቅ እንድንዘጋጅ ይረዳናል፡፡ ይህም የእኛ ትኩረት በተለየ መልኩ እነርሱ ላይ ባይሆንም እንኳን የሠዎችን ተነሳሽነት እና ሀሳብ ለማግኘት ያግዛል፡፡ በዚህ አይነት መንገድ የእኛ ስሜት ጥንካሬያችን ይሆናል፡፡ ለሌሎች ያለን ስሜት ውስጣችንን ንቁ በማድረግ ስለሌሎች በደመነፍስ እንዳናስብ እና ማንኛውንም የስሜት መቀየርን ማዳመጥ ወይም በስራ አካባቢ ያለውን አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እንድናውቅ ያግዘናል፡፡ ሠዎችን ያለምንም ማስረጃ ማመን መቻል በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በመስተጋብር ጊዜ ምን
ያህል ስኬታማ ለመለካት ያግዘናል፡፡

 

4. ተርÕሚ ቃላቶችን መጠቀም
ብዙ ሠዎች ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ንግግር ያደርጋሉ ይህም በስትክክል ምን ለማለት እንደፈለጉ እንዳንረዳ ያደርጋል፡፡ በተለይ የጽሁፍ መልክት በምታስቀምጡ ጊዜ ብዙ አይነት የአተረÕጎም ችግር ያጋጥማል፡፡ ሁሉም ሠው ሁልጊዜ የሚናገረው ማለት የፈለገውን እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ በስራ ቦታ፤ እያንዳንዱ ሠው ተገቢ ካልሆን ትችት ይልቅ የሌሎችን ፍላጎት ለማሟላት እና ሀሳብን ለመጋራት እንዴት በነጻነትና በጋራ ጥረት እነደሚያከናውን እናያለን፡፡ ለመናገር ወይም ላለመናገር የወሰነውን ውሳኔ በሌሎች ሠዎች ዘንድ በተቻለን አቅም በትክክለኛው መንገድ መተርጎም መቻላቸውን ማወቅ አለብን፡፡ ካልገባን እና ትክክለኛውን ሀሳብ ማግኘት ካልቻልን ለመግባባት ግልጽ የሆን ውይይት ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ብዙዎቹ ግጭትን የሚያስነሱ ሁኔታዎች ሌሎች ሠዎች ለመግባባት በሚሞክሩበት የአተረÕጎም ችግር ነው፡፡ ንግግራቹ አንድ ጊዜ ግልጽ ከሆነ እምነትን ታተርፋላቹ ስኬትም የእናንተ ትሆናለች፡፡

5. ልዩ የሆነ አክብሮት
የሠዎችን አመለካከት መቀበል አስፈላጊ የሚሆነው እውቀትን ለማዳበር ያለን ችሎታ እና ለሌሎች ሠዎች ግላዊ እምነት ያለን አክብሮት ነው፡፡ ለሠዎች ክብርን እና እምነትን የምንነፍግ ከሆነ እርስበርስ የመለያየትና የመከፋፈል መንገድን እንገነባለን ይህም የስራ ባልደረባን፣ ደንበኛንም ሆነ አለቃን የማነሳጫ መንገድ ነው፡፡ በአለም ላይ ያለው ሁሉም ሰው ግላዊ ምልከታችንን እና እምነታችንን ይጋራል ብሎ ማሰብ ከባድ ይሆናል ግን ሠዎች ሲቀርቡአቹ ግልጽ በሆነ አዕምሮ የእነርሱን እምነት አክብሮት ልምዳቹ አድርጉ፡፡ ይህም ማለት መናገር ያለባችሁን እንደምታውቁ ሁሉ መናገር የሌለባችሁን መለየት ይጠበቅባችኃል ይህ ትንሽ ግንኙነትን ውስብስብ ያደርገዋል ግን ግልጽ እና የበሰለ አዕምሮን እንድታዳብሩና ለሌሎች አክብሮት እንድታሳዩ መንገድ ይከፍታል፡፡


6. ሠዎችን ማወቅ
ሠዎች ከየት እንደመጡ እና አሁን ያላቸውን ማንነት እንዴት እንዳገኙ በጥልቅ የምታውቁት ከሚናገሩት እና ከሚያከናውኑት ነገሮች ነው፡፡ በስራ አለም ላይ ብዙ የስራ ልምድ ያለውን እና አዲስ ተቀጣሪ የሆኑትን ባልደረቦቻችንን በማወዳደር የተለየ ግምት እንጣቸዋለን ይህም አዕምሮአችን ባፋጣኝ በሚፈለገው አቅጣጫ ይመራናል፡፡ በንግግር ጊዜ ሠዎች አዕምሮአችንን መንበብ ሲችሉ ግራ ሊያጋባን ይችላል ለዛም ነው ያለንን ሀሳብ ብዙ መግለጽ ይኑርብን ወይም ትንሽ ማካፈል ይኑርብን ስለማናውቅ እቅዳችንን ያደናቅፍብናል፡፡ የንግግርን ስህተቶች ለመቅረፍ ሠዎች በደንብ እንድናውቃቸው ይፈልጋሉ፤ ነገርግን ምንም ያህል ብናውቃቸው ሠው ነንና ከመሳሳት ላንድን እንችላለን፡፡ በእንደነዚህ አይነት ስህተቶች ውስጥ እያለፍን እያንዳንዱ ግንኙነታችንን አመዛዝነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ እያንዳንዱ ስህተት ስኬታችንን የተሻለ እና ያለንን ግንኙነት አዕምሮአችንን በመጠቀም እድገት እንድናሳይ ያደርገናል፡፡


7. የእያንዳንዱን ሠው ማንነት መመርመር
ከሁሉንም ሠው ጋር መተዋወቅ እና ተዛምዶ መፍጠር ያስደስታል፤ ነገርግን እኛ አንድን ሠው የምንዛመድበት መንገድ እንዴት ሠዎችን ልንረዳቸው እንችላለን የሚለውን ከግምት ውስጥ መክተት ይኖርብናል፡፡ ኮስታራ እና ምሁር ከሆኑ የስራ ባልደረቦቻችን ጋር ስንሆን የተለየ የመስተጋብር ዘዴዎች እንጠቀማለን በአንጻሩ ግን ያለንን ቅርበት ለተረጋጋ እና ቀለል ለሚለን
ሠው ትኩረት እንሰጣለን፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ ሁላችንንም ማህበራዊ ጉዳዮች ያስተሳስሩናል፡፡ ባህሪያችንን በጥቂቱ ዘንበል ማድረግ ከሠዎች ጋር እንድንስማማ እና ያለን ጥሩ ማንነት እንዲያስተሳስረን ያደርጋል፡፡ ይህ ማህበራዊ ስምምነት በዙሪያችን ላሉት ሠዎች በአግባቡ ከተገበርን የተሳሳተ ግምት እንዲሰጡን አያደርግም፡፡ ያለንም ማንነት በተለያየ መንገድ አዎንታዊ እና ውጤታማ ግንኙነት እነዲኖረን ይመራናል፡፡ ይህ አይነት ሽግግር ከሌሎች ሠዎችም ጋር ሆነ ከራሳችን ጋር ስኬትን ያላብሰናል፡፡

የሌሎችን አስተሳሰብ መውሰድ መልመድ በስራ ላይ የርህራሄ መንፈስ እነዲኖረን ያደርጋል ይህም ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነት በጣም ጥሩ በሆነ አቅም አዎንታዊ ገጽታን ያሳድርብናል፡፡ ስለ ርህራሄ ስናስብ በተፈጥሮ፤ መልሳችንን ሠዎች እንዴት ይረዱታል ብለን እንድናሻሽል እና አስተያየትን ከሠዎች እነድናገኝ ያደርጋል፡፡ ሠዎች አስተያየት ሲሰጡን እውነት ለመናገር በጊዜው የእኛ መልስ በቅሬታ እና በቁጣ የተሞላ ሊሆን ይችላል ይህም ማለት የስኬት መንገዳችንን ሊያበላሽብን ስለሚችል በተቻለን አቅም መልካሙን መንገድ መምረጥ ይኖርብናል፡፡ ስኬት በሂወታችን ውስጥ ሲካተት እና ውጤታማ መስተጋብር ሲኖረው፤ ሰብአዊነት፣ ግላዊ እውቀት እና ስለአመለካከት መቀበል ችሎታ አስፈላጊነት በሚገባ እናውቃለን፡፡ እነዚህ ባህሪዎች የሁሉም አይነት የስኬት ቁልፍ ናቸው፡፡