Blog > Self Development

ውጤታማ ስራ ፈጣሪ ለመሆን የሚያግዙ 8 ልማዶች

ስኬታማ ለመሆን ውጤታማነት ለምን በጣም አስፈላጊ ይሆናል? ምክንያቱም በእያንዳንዱ የውሳኔያችሁ ሂደት ላይ ውጤታማነታችሁ ዋናውን ሚና ይጫወታል፡፡ ውጤታማ መሆናችሁ ምኞታችሁን ለማሳካት ይጠቅማችኃል፡፡ አብዛኞቹ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች በውጤታማነት የተካኑ ናቸው ምክንያቱም በብልጠት ስለሚሰሩ፣ አላስፈላጊ ጥረትን ስለሚያስቀሩ እና ጊዜያቸውን ስለማያባክኑ ነው፡፡ ፅኑ አም ከሌለ እና በአጋጣሚዎች ስኬታማነትን ማግኘት አይቻልም፡፡ አብዛኞቹ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች በቀላሉ አይወድቁም ወይም በውሳኔያቸው ሂደት ላይ መዝረክረክ አይታይባቸውም ምክንያቱም ከውሳኔያቸው በፊት ግባቸውን በጥልቅ የመመልከት፣ የማዋቀር እና ሙሉ በሙሉ የመዘጋጀት ልምድ ስላላቸው፡፡   

እነዚህን ውጤታማ ስራ ፈጣሪ ለመሆን የሚያግዙ 8 ልማዶች ብታዳብሩ በአዎንታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ መቆየት ትችላላችሁ፡

1. እይታ

አብዛኞቹ ተፅኖ ፈጣሪ ስራ ፈጣሪዎች እያንዳንዱ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በማሰብ እና እይታቸውን በማስፋት ነው በተፈጥሮም ሚ በሆኑ ሂደቶች ላይ አዲስ ነገሮችን የመፍጠር እና የመታመን እድል አላቸው፡፡ የሚያፈልቁትም ሀሳብ በከፍተኛ ደረጃ ዋጋ ያለው ነው፡፡ ሁልጊዜም ጎበዝ ህልመኞች እና ህልማቸውን ተግባሪ ሲሆኑ ይህንን ስጦታ የታደሉ ሰዎች ትልቅ ህልም ከሌላቸው ሰዎች የተገለሉ ናቸው፡፡ ህልማችን መቆሚያ የለውም ብለው የሚያስቡ ሠዎች የፈጠራ ችሎታቸው፣ ስኬታቸው፣ ገንዘብ የማግኘት ዘዴያቸው፣ ስጋትን መቆጣጠሪያቸው እና ያመኑበትን በማፈፀም የታደሉ ናቸው፡፡ አንድ ነገር ጨርሰው የሚቆሙም አይደሉም፡፡

2. በጠዋት መንቃት

ውጤታማ ስራ ፈጣሪዎች በፍጥነት የሚያድጉት ያሰቡትን ለማሳካት ስለሚደክሙ ነው፡፡ እያንዳንዱን ቀን የሰውነት እንቅስቃሴ በማድረግ ይጀምራሉ ይህም እራሳቸውን ንቁ የሚያደርጉበት፣ ደማቸውን የሚያሞቁበት እና አዕምሮዋቸውን ዝግጁ የሚያደርጉበት ዘዴ ነው፡፡ ለቀን ያዘጋጁትን ግብ ለማሳካት ሀሳባቸውን ሰብስበው እንዲሰሩ ሌሎች ሰራተኞች ከመግባታቸው በፊት ቀድመው መግባትን ይመርጣሉ፡፡ በጠዋት መነሳት ድብርትን የማስወገድ ከፍተኛ አቅም አለው፡፡ አካባቢያችሁ ፀጥ ሲል እና ከሁካታ ነፃ ሲሆን ስራችሁን በጥራት እና በስኬት ለመፈፀም ያግዛችኃል፡፡ በጠዋት ቢሮ መግባት ከሚሰጣቸው ጥቅሞች መካከል ሌላኛው ከስራ ባልደረቦቻችሁ ጋር በቂ ጊዜ የምታሳልፉበት እና የምትተጋገዙበት ጊዜ ታገኛላችሁ፡፡

3.ማቀድ

ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች ብቁነታቸውን የሚያሳድጉት ለስራቸው ቅድሚያ በመስጠት እና ማህበራዊ ህይወታቸውን በማስከተል ነው፡፡ ማህበራዊ ህይወት በጣም አስፈላጊ እና ህይወት የሚያሰጥ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ከሠዎች መራቅ የሚያስከትለው ዋጋ ከባድ ነው ምክንያቱም ሠዎች በዙሪያችሁ ሲኖሩ ጭንቀት እንድታስወግዱ እና የፈጠር ችሎታን እንድትጨምሩ ያደርጋል፡፡ በአብዛኛው የስራ ጫናችሁን ከጨረሳችሁ በኃላ ማህበራዊ ህይወታችሁን የምታሳኬዱበት እቅድ ማውጣት አለባችሁ፡፡ ይህም ትስስርን እና ግንኙነትን ለማዳበር ይረዳችኃል ምክንያቱም ህይወታችሁን በምትፈልጉት እና በመረጣችሁት መንገድ እንድትመሩ ስለሚረዳ፡፡   

4. መተኛት

ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች በጭራሽ የእንቅልፍን አስፈላጊነት አይዘነጉም፡፡ ንቁ የመሆን፣ በስሜት የመገኘት እና በስራቸው ላይ ሙሉ በሙሉ የመሳተፍ ፍላጎት አላቸው፡፡ በእንቅልፍ እና በድብርት መካከል ያለውን የተለያየ አቅጣጫ የሚያረጋግጥ ሰነድ እንደሚያሳየው እንቅልፍ ማጣት የስሜት አለመነቃቃትን እና ብስጭትን እንደሚያስከትል ነው ይህም ለሌላ የእንቅልፍ እጦት እንድንጋለጥ ያደርጋል፡፡ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች ማታ ማታ ቀን ያሳለፉትን አድካሚ ሁኔታዎች እና ከሠዎች ጋር የነበራቸውን መስተጋብር እያሰቡ የእንቅልፍ ጊዜያቸውን ማባከን አይፈልጉም፡፡ በቂ እንቅልፍ እማታገኙ ከሆነ ውጤታማነት የማይታሰብ ነው፡፡ ስራችሁ የትም እንደማይሄድባችሁ ማመን አለባችሁ፡፡ ሁልጊዜም ለእንቅልፋችሁ አስፈላጊውን ጊዜ መስጠት እና ምቹ ማድረግ ይጠበቅባችኃል፡፡ ይህንን የማታደርጉ ከሆነ ግን ብቁነትን ለመቀነስ፣ ጤናችሁን ለማጣት እና ስራችሁ ለማቃወስ ትጋለጣላችሁ፡፡      

5. ነገሮችን ቀለል አድርጎ መመልከት

ነገሮችን ቀለል ማድረግ የስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች መገለጫ ነው፡፡ የቀን ተቀን ህይወታቸውን በቀላል መንገድ መምራት እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ቀለል ያለ ህይወት መምራት መቻል የስራን ጫናን ከመቀነስ ባሻገር ሀላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት ያግዛል፡፡ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች ምንም አይነት ጭንቀት ሳያድርባቸው የምኞታቸውን ውጤት የማየት ከፍተኛ ጉጉት አላቸው በዚህም ምክንያት በዙሪያቸው ላሉ ነገሮች ገደብ ያስቀምጣሉ፡፡ የሚያስጨንቃቸው ሰለሠዎች ሳይሆን ከፍተኛ ጥራት ያለውን ስራ መስራት መቻላቸው ነው፡፡ የሚያስቀምጡት ገደብ የሚሰጣቸው ጥቅም ለህይወታቸው ወኪል ማግኘትን፣ የስራ ጫናን ለመቀነስ እና ስራቸውን በቅልጥፍናና በውጤት እንዲያከናውኑ ያደርጋል፡፡

6. ማስታወሻ መያዝ

ውጤታማነትን በቀላል መንገድ ለማዳበር የቀን ውሎአችሁን በማስታወሻ ላይ የማስፈር ልማድ እንዲኖራችሁ ማድረግ ነው፡፡ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች ብዕራቸውን ከወረቀት ጋር በማገናኘት ለእነርሱ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች በሙሉ ያሰፍራሉ፡፡ የግባቸውን ዝርዝር ማውጣት ወይም የምዘና መስፈርታቸውን መፃፍ ያዘወትራሉ፡፡ መፃፍ አያሌ ጥቅሞች እንዳሉት መቼም አያዘነጋም፤ የአዕምሮአችሁን ክፍሎች በማስተሳሰር ችግሮችን መፍታት እንድትችሉ እና አዲስ ነገር የመፍጠር ልምዳችሁን እንድታዳብሩ ያደርጋል፡፡ ከዚህም በላይ ስሜታችሁን በሚገባ ለመግለፅ፣ በጭንቀት እንዳትሞሉ እና ከተለያዩ የኤሌክትሪክና የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች እንድትርቁ ያግዛል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ ውጤታማ የሆኑ ስራ ፈጣሪዎች ለፅሁፍ ትልቅ ዋጋ ይሰጣሉ ምክንያቱም ከህይወታቸው አካሄድ ጋር እንዲያስተሳስራቸው እና የጥረታቸውን ውጤት ማየት እንዲችሉ ያደርጋል፡፡

7. ዝንባሌ

እንደ ልምድ ሆኖ ውጤታማ ስራ ፈጣሪዎች አጋጣሚዎችን ለመቀየር እና ሀላፊነትን በአጋባቡ ለመወጣት ዝንባሌ አስፈላጊ እንደሆነ በደንብ ይረዳሉ፡፡ በበቂ ሁኔታ ዝንባሌን ለይቶ ማወቅ አቅጣጫን በአስገራሚ ሁኔታ በመቀየር ስኬትን ይጨምራል በተጨማሪም መማርን፣ እድገትን እና እውቀትን ለማስፋፋት ጠቃሚ ነው፡፡ የሚኖሩበት የህይወት ሂደት የተለመደ እና ቀለል ያለ ነው ምክንያቱም ሁኔታዎችን በቀላል መንገድ ለማስተዳደር ምቹ ስለሆነ፡፡ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች አስፈላጊ ባልሆነ ነገር ላይ ልምድ የላቸውም ይህም ምርታማነትን ይጨምራል ምክንያቱም ለስራ ያላቸው ግምት እና ከስራቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት የተለየ ቦታም ላይ ቢሆኑ ለመስራት አያግዳቸውም፡፡             

8. የማወቅ ፍላጎት

ስልቹነት ውጤታማነት ገዳይ ነው ለዛም ነው አብዛኞቹ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች የማይሰለቻቸው፡፡ ምንጊዜም የስራ ጊዜያቸውን በደስታ እና በፍቅር ነው የሚያሳልፉት፤ በሁሉም ነገሮች ላይ ግልፅነትን እና ጉጉትንም ልማድ አድርገው ይዘውታል፡፡ ይህ የማወቅ ፍላጎት ለሚቀጥለው ስራ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ እና ሀሳቦችን እንዲያፈልቁ ይረዳቸዋል፡፡ በማንኛውም ጊዜ የተወሰነም ሀሳብ ቢሆን ሳይዙ መቅረብን አይሹም ለስኬታማነታቸው እና ለውጤታማነታቸው ያላቸው ጉጉት ትልቁን ሚና እንደሚጫወትም ያምናሉ፡፡ አማካኝ ደረጃ ላይ ያሉ ሠዎች የፈጠራ ችሎታቸው ሲደክም ይሸሻሉ በከፍተኛ ደረጃ ብቁ ናቸው የሚባሉት ስራ ፈጣሪዎች ግን አዲስ ሀሳብ ለማፍለቅ እና የተሻለ አቅጣጫን ለመÕዝ ይተጋሉ፡፡