Blog > Self Development

ከተከታይነት ወደ መሪነት የሚያደርሱ መንገዶች

እራሳችሁን ተከታይ አድርጋችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ሁልጊዜም መሪ ለመሆንስ ፍላጎት አድሮባችሁ ያውቃል? ተከታይነት እና መሪነትስ በምንድነው የሚለያዩት?

መሪነት ከተጨማሪ ሀላፊነት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ነው ግን ተጨማሪ እድሎችን፣ ተጨማሪ ክብርን እና ካቅማችሁ በላይ የሆን ቁጥጥር ይዞ ይመጣል፡፡ አንዳንድ ሠዎች መሪነትን ይሸሻሉ፤ እንደያስፈላጊነቱ በትልልቅ ቦታዎች ላይ ማገልገል ከባድ ሲሆንባቸው የተቀሩት ህይወታቸው እና እጣፈንታቸው እንዲቀየር እድገትን ይመኛሉ፡፡ ግን ያላችሁን ህይወት ተቀብላችሁ ትኖሩ ከነበረ እና በስራ መስካችሁ ላይ እንደ ተከታይ ካሳለፋችሁ መሪ ለመሆን ይቻላችኃል?  

እንዴት መሪ መሆን ይቻላል?

መሪዎች ልክ እነደማንኛውም ሠው ተወልደው እንጂ ተሰርተው አይደለም ግን ስኬታማ የሚያደርጋቸው ምን እነደሆነ እንመልከት፡-

 • በራስ መተማመን፡- አንዳንዶች በተፈጥሮ የሚታደሉት ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ያሰቡትን እስኪተገብሩ ድረስ የሚያስመስሉበት ዘዴ ነው፡፡ መሪዎች በራስ የመተማመን ገጽታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ውስጣቸው ያለውን ስሜት አምቀው ማሳተፍ የሚገባቸው ብቃት በራስ መተማመናቸውን ነው፡፡
 • እውቀት፡- አንድ ሠው ማግኘት አለበት የሚባል የእውቀት ገደብ የለም ስለዚህ ሊደረስበት የማይችል ነገር የለም የሚል ስንቅ ይዘው ይÕዛሉ፡፡
 • ተሰጥኦ፡- ችሎታን በልምምድ ማሻሻል ይቻላል፡፡ ሁልጊዜም ላላችሁ የስራ ቦታ ተስማሚ ካልሆናችሁ የተሻለ ለመሆን ትተጋላችሁ፡፡
 • ወሳኝነት፡- ይህም በብዛት ለአንዳንድ ሠዎች በተፈጥሮ የሚገኝ ሲሆን ለሌሎች ግን ከፍተኛ ችሎታን ይጠይቃል፡፡ ትልልቅ ውሳኔዎችን መወሰን፣ ለመፍትሄው መጣር መለማመድ እና መሻሻል የሚችል ነው፡፡
 • አክብሮት፡- ተከታይም መሪም ብቶኑ አክብሮትን ለሁሉም ሠው ማሳየት ተገቢ ነው፡፡ ይህንንም በአግባቡ ካልተገበራችሁ መሪ የመሆን መብትን አታገኙም፡፡
 • ቁርጠኝነት፡- መሪ የመሆን ፍላጎት ካላችሁ በትንሹም ቢሆን ግባችሁን እና ሀሳባችሁን ካሁኑ ፈጽማችኃል ማለት ነው፡፡
 • መግባባት፡- አንዳንድ ሠዎች በተፈጥሮ ቅርበት እና ግንኙነት ለመፍጠር የታደሉ ቢሆኑም አንዳነዶቹ ደግሞ የሚኖራቸው የግንኙነት ችሎታ በልምምድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ይህ አንድ መሪ ሊኖረው የሚገባ መሰረታዊ ሀሳቦች አጠቃላይ ዝርዝር ነው፡፡ እንደተገነዘባችሁት ሁሉም በግልጽ ተቀምጠዋል በቀላል መንገድም የሚገኙ ናቸው ላይገኙ ቢችሉ እንኳን በትክክለኛው ተነሳሽነት መሪ መሆን እንደሚቻል ይገልጻሉ፡፡      

 

መሪነትን መሳተፍ

መሪ መሆን መገኘት የሚችል ስልጣን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ መሪነትን እንዴት ማግኘት እንደምትችሉ የሚጠቅሙ 4 ዘዴዎችን እናካፍላችሁ፡-

 1. ልምድ፡- ይህ የመጀመሪያው ዘዴ ሲሆን በቀላሉ ስልጣንን ያስገኛል፡፡ ውስን በሆኑ ኢንዱስትሪ ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ ከተሳሰራችሁ፣ ለነበራችሁ የስራ ድርሻ ተስማሚ ከሆናችሁ ወይም ጥሩ ሚና ከተጫወታችሁ የተሻለ ልምድ የመያዝ እድሉ ይኖራችኃል፡፡ የስራውንም ውስጣዊ እና ውጫዊ አለም ታውቃላችሁ በተለይ በሌሎች አካባቢዎች ስላለው የስራ ሁኔታ የምታውቁ ከሆነ እና እውቀትን ከተጋራችሁ የግንኙነት ችሎታ እና ስኬታማ ለመሆን ያላችሁ በራስ መተማመን ለመሪነትም ተስማሚ ቦታን ያስገኝላችኃል፡፡ ይሄ የመጀመሪያው የመሪነት መንገድ ሲሆን ጠንክሮ መስራት መቀጠል እና እራስን ማሻሻል በመጨረሻም ለስራችሁ ተገቢውንና ትክክለኛውን ቦታ እንድታገኙ ያግዛችኃል፡፡
 2. የስራ እድገት፡- ባንድ ጊዜ ከተከታይነት ወደ መሪነት መሄድ አይጠበቅባችሁም፡፡ እንደውም በሁለቱም መካከል ያለውን የሚያስተናግድ ብዙ ሙያዊ አቅጣጫ አለ፡፡ ለዚህም ማናጀሮችን እንደ ጥሩ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን፤ ጥብቅ የሆነ ውሳኔን ይወስናሉ፣ የድርጅቱ አላማ ለማሳካት የራሳቸውን ቡድን ያዋቀሩ ናቸው፡፡ ይህንን የመሪነት ሚና ለማግኘት መሸጋገሪያ ፍለጋ መጣር፣ ለቦታው ተስማሚ ሠው ለመሆን መሰላል ማበጀት የመሪነት ደረጃ ላይ ለመድረስ እድል ያመቻቻል፡፡
 3. ግልጽ ፍላጎት፡- የመሪነት ችሎታን ማበልጸግ የሚቻለው የፍላጎት ግፊት በግልጽ ስላለ ነው፡፡ ታታሪ ከሆናችሁ፣ በቁጥጥር እና በምዘና ላይ የተወሰነ ስልጣን ካላችሁ መሪ ለመሆን የሚጠበቅባችሁን አደረጋችሁ ማለት ነው፡፡ ቀስ እያላችሁም ሁሉም አይነት የችሎታ ዝርዝር ላይ መድረስ ትችላላችሁ ወይም ማግኘት ያለባችሁን እውቀት ታገኛላችሁ ያኔም በቀስታ ለመተግበር እድሎች ይመቻቹላችኃል፡፡ ይህ ዘዴ የተወሰነ ጊዜና ጉልበት ቢወስድም ወደ ትክክለኛው የእድገት ጎዳና ይመራል፡፡
 4. አስፈላጊነት፡- አንዳንድ ጊዜ ዋና ለመልመድ አስፈላጊው መንገድ ውሃ ውስጥ ሰርጎ መግባትን ማወቅ ነው፡፡ እንደ መሪ ችሎታን በፍጥነት በልምድ ማሳደግ ይቻላል በሌላ በኩል ደግሞ መሪነትን መላመድ አስፈላጊ ነው፡፡ ማለትም የራስን ስራ ለመጀመር ‘’ምን ያህል ዝግጁ ነኝ?’’ ብሎ ራስን መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ ፈጣን የመሪነት ስልጣን በራሱ አስፈሪ ነው ግን የሁኔታዎች ግፊት አስፈላጊ ልምዶችን በፍጥነት እንድናሳድግ ይረዱናል፡፡

መሪ ለመሆን የሚያነሳሱን ከላይ የገለጽናቸው ስልቶች ብቻ አይደሉም፤ ነገርግን በጣም ፈጣንና ዋና ዋናዎቹ ናቸው በተለይ መንገድ ለመምረጥ፣ ውጣውረዶችን ተቋቁሞ የተሻለ ነገር ለማግኘት ይረዱናል፡፡ በውሳኔያችሁ ከጸናችሁ፣ ፈተናዎችን መጋፈጥ ከቻላችሁ ጥሩ መሪ ከመሆን የሚያግዳችሁ ነገር አይኖርም፡፡