Blog > Self Development

አሁን ያላችሁን ስራ እየሰራችሁ የራሳችሁን ስራ የምታሳኩበት 7 መንገዶች

ብዙ ሰዎች ህልማቸው የሆነውን የራሳቸው ስራ ለመጀመር ተግተው ይሰራሉ፡፡ አብዛኞቹ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች አሁን ያሉበት ስኬታማ ቦታ ለመድረስ የነበራቸውን ስራ በአግባቡ እና በትጋት ይሰሩ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት የስኬት መንገድ ላይ ለመድረስ ግን ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ አይሆኑም በተለይ ስራቸው የማያስደስታቸው ከሆነ ብዙ ጭንቀት እና አስቸጋሪ ጊዜያቶችን ያሳልፋሉ፡፡

ምኞት በጣም አስፈላጊ ነው፤ ሁልጊዜም ግን ወደፊት ለመጓዝ ምኞት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ያላችሁን ተነሳሽነት ለመምራት እና ከተቀጣሪ ወደ ስራ ፈጣሪ በጊዜው ለመድረስ እንደግብ ማስቀመጥ አለባቹ፡፡ አቅጣጫን መለወጥ ከባድ እና በሂደቱ ላይ ተስፋ መቁረጥ የተለመደ ነው፡፡ አሁን ያላችሁ ስራ ወደፊት አንድ እርምጃ እንዲያራምዳችሁ ባፋጣኝ ልትወስዷቸው የሚገቡ ውሳኔዎች አሉ፡-

1. የራሳችሁን ስራ ለመጀመር ያነሳሳችሁን ምክንያት በግልጽ ማወቅ

 

ምንግዜም “ለምን?” የሚለው ጥያቄ አንድ እርምጃ ለመራመድ አስፈላጊ ነው፡፡ ምናልባት ለአላማችሁ መነሳሳት ምክንያት እንዲሆን፣ ጥገኛ ላለመሆን፣ የጊዜው ነጻነት በመፈለግ፣ የፈጠራ ችሎታን ለማዳበር፣ ከልጆቻችሁ ጋር በቂ ጊዜ ለማሳለፍ እና ሌሎችን ለመርዳት ይሆናል፡፡ ምክንያታችሁ ምንም ይሁን፤ ምን እንዳነሳሳችሁ እና ትኩረታችሁን ምን እንደሳበው ማወቃችሁ አስቸጋሪ ጊዜያቶችም ሲጋጥሟችሁ ህልማችሁን ለመፈጸም ስንቅ ይሆኑአችኃል፡፡

 

2. ህልማችሁን እውን ለማድረግ መጣር

 

ስራ ለመስራት ምኞት ማሳደር እና ስራውን መፈጸም እጅግ ይለያያል፡፡ ህልማችሁን ለመፈጸም ስታስቡ ስኬታማ ሆኖ ለማየት መጽናት ይኖርባችኃል፤ ይህም ማለት ሙሉ ለሙሉ ትኩረት መስጠት አለባችሁ፡፡ በመሰናክሎች ብትሞሉ እንኳን ምንም ነገር ተጋፍጣችሁ የመቀጠል ልምድ ይኑራችሁ፤ ለራሳችሁ ቃል በመግባት በሂወታችሁ ውስጥ ላሉ ሠዎችም ህልማችሁን አካፍሏቸው፡፡

 

3. ለስራችሁ የሚሆን ግላዊ እይታ መፍጠር

 

ያሰባችሁት ስራ ከአመት በኃላ የት እንደሚደርስ ማሰብ እና በግልጽ አብራርቶ በጽሁፍ ማስቀመጥ ይኖርባችኃል፡፡ ይህን ማድረጋችሁ ትልቁ ጠቀሜታ፤ የትኞቹ እንቅስቃሴዎች እጩ እንደሆኑ፣ ምን ያህል ደንበኞች እንዳላችሁ እና የወር ገቢያችሁ ምንያህል እንደሆነ ለማወቅ ይጠቅማችኃል፡፡  

 

የጻፋችሁትን ሁልጊዜም ጠዋት ጠዋት እና ማታማታ አንብቡት፣ ግባችሁን ለማሳካት ጥረት አድርጉ፣ ስራችሁን አበልጽጉ፡፡ በውጤቱ ላይ ማተኮር መቻላችሁ በቀን ተቀን ኑሮአችሁ ላይ የሚያጋጥማችሁ ማንኛውም አሉታዊ ሀሳቦችን እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡

 

4. የምሁሮች ህብረት ውስጥ መካተት

 

የምሁሮች ስብስብ ውስጥ መደበኛ የሆነ ስብሰባ በማካሄድ እርስ በእርስ መደጋገፍ፣ ትልልቅ ሀሳቦችን እና ምክሮችን በማጋራት የሚያጋጥሟቸውን ውጣውረዶች መጋፈጥ፡፡ እንዲህ አይነት ህብረት ውስጥ መካተት ተጠያቂነት እንዲሰማችሁ እና እንዲያነቃቃችሁ ያደርጋል፡፡

 

የምሁሮች ህብረት በአካል፣ በድረ ገጾች እና በስልክ ማካሄድ ይቻላል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ህብረቱን ለማሰባሰብ በስራቸው ጥሩ ስም ያላቸውን ሠዎች ማሰባሰብ፤ ተካፋይ የሚሆን ካጣችሁ የራሳቸውን ስራ የጀመሩ ሠዎችን አፈላልጋችሁ ቡድን መመስረት ትችላላችሁ፡፡

 

5. ትምህርት ውስጥ እራሳችሁን መዝፈቅ

 

ለስራችሁ ጠቃሚ ነው ብላችሁ የምታስቡትን ማንኛውንም ምርምሮች እና ጥናቶች መመልከት አለባችሁ፡፡ ስኬታማ ስራን ለመመስረት ድረ ገጾችን መመልከት ከመጠን በላይ ዋጋ ያለው መረጃ ይሰጣችኃል፤ ስልጠናዎችን መውሰድ፣ አሰልጣኝ መቅጠር እና ከአዋቂ ሠዎች ጋር መገናኘት አለባችሁ፡፡ ጠዋት ስትነሱ በድምጽ (በራዲዮ) የሚሰጡ አጋዥ የሆኑ ዝግጅቶችን ማዳመጥም አንዱ ትምህርት የማግኛ መንገድ ነው፡፡ ስለአካባቢያችሁ ብዙ ባወቃችሁ እና ባለሙያ በሆናችሁ ቁጥር በራስ መተማመናችሁ በመጨመር እና በመነቃቃት በቀላሉ ስኬታማ ትሆናላችሁ፡፡

 

6. አሁን ላላችሁ ስራ አዎንታዊ አመለካከት ማሳደር

 

በየቀኑ ስራችሁን ሊያበረታታ የሚችል ነገር አስቡ፤ ምናልባት ከስራ ባልደረቦቻችሁ ጋር መዝናናት ወይም የበአል እረፍቶቻችሁን አብሮ በጋራ ቡና በመጠጣት የተሻለ ጉርብትናን መፍጠር ይቻላል፡፡ ዋናው ነገር ጥሩ ነገሮችን መመልከት መቻላችሁ ነው፡፡ ሁልጊዜም አሁን ላላችሁበት ሁኔታዎች አዎንታዊው ላይ ብቻ ካተኮራችሁ ስራችሁን ጨምሮ ላለው ጊዜያዊ ሁኔታ ስኬትን ታመጣላችሁ፡፡ አሉታዊ ሀሳቦች ያላችሁን እምቅ ሀይል ያጠፉባችኃል፤ ህልማችሁንም ለማሳካት እንዳትÕዙ መንገዱን አስቸጋሪ ያደርግባችኃል፡፡  

 

7. የቀን ግብ ይኑራችሁ

 

ስራችሁን ወደፊት የተሳካ ለማድረግ አንድ እርምጃ ማራመድ እና በእድገት ጎዳና ለመÕዝ ያላችሁን ጊዜ ባግባቡ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ስራችሁን ስትጀምሩ ውጥረት ካለባችሁ በቀን ተቀን ስራ ላይ ድብርትን ያመጣል ግን በየጊዜው የተወሰነ በመስራት በየቀኑ አንድ እርምጃ መራመድ ውጤቱን ባፋጣኝ ለማስገኘት ያግዛል፡፡ ረጅም የእድገት ጎዳና በተÕዛችሁ ቁጥር ወደፊት ለመራመድ በራስ መተማመንን እና ቁርጠኝነትን ያላብሳችኃል፡፡

 

አሁን ያልችሁን ስራ እየሠራችሁ እነዚህን ክንውኖች ከፈጸማችሁ፤ ትኩረት እንዳረጋችሁ ትቆያላሁ፣ ተነሳሽነት ይኖራችኃላ፣ ህልማችሁንም ለማሳካት መንገድ ይከፍታል ስለዚህ አሁን የምትሰሩትን ስራ እንደ መሸጋገሪያ ድልድይ እና እንደ ጊዜ ማሳለፊያ ይሆናችኃል፡፡