Blog > Self Development

ቤተሰባችሁን እና ስራችሁን አመዛዝናችሁ ለማስኬድ የሚያግዙ 5 በጣም አስፈላጊ መንገዶች

ቤተሰብን እና ስራን አመዛዝኖ ማስኬድ ከባድ ቢሆንም ግን ጊዜያችሁን ባግባቡ ከተጠቀማችሁ ሁሉም ቀላል ይሆናል፡፡ እነዚህን 5 እቅዶችንም በማውጣት እንዴት አጣጥማችሁ መÕዝ እንዳለባችሁ ለማወቅ ያግዛል፡፡

 

  1. ከእቅዶቻችሁ መካከል የቤተሰብ ጊዜን መስርቱ

አብዛኛውን ጊዜ ከ3 እስከ 11 ሰዐት በስራ ገበታ ላይ ታሳልፋላችሁ፤ ታዲያ ለቤተሰባችሁ የምትሰጡት ጊዜ በየትኛው ሰዐት ነው? የራሳቸውን ስራ የሚሰሩ ብዙሀኑ ህብረተሰብ ስራቸው አልቆ ከቤተሰባቸው ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ ይናፍቃሉ፡፡ ይህንንም ለመተግበር ቀላል የሚሆነው በቀን ውስጥ ያላችሁን ስራ ባግባቡ እና በጊዜው መፈፀም ስትችሉ ነው፡፡

ለቤተሰባችሁ በቂ ጊዜ የማትሰጡ ከሆነ ህይወት ባስጨነቀቻችሁ ጊዜ ቀዳሚ ወዳቂዎች ናችሁ፡፡ በሳምንት ውስጥ ግዴታ ለቤተሰባችሁ የምትሰጡት ጊዜ ሊኖር ይገባል፤ ይህንን በመደበኛነት የምትተገብሩ ከሆነ እራሳችሁንም ሆነ ቤተሰባችሁን ደስተኛ አድርጋችሁ መቆየት ትችላላችሁ፡፡ በተለይ የትዳር አጋራችሁን የልደት ቀን፣ የተገናኛችሁበትን ቀን እና የልጆቻችሁን ልዩ ልዩ ቀናቶች በአንድ ልይ ተሰባስባችሁ ማሳለፍ ይኖርባችኃል፡፡ በተጨማሪም የቤተሰብ ስብሰባ ማድረግ፣ ባለው ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ መነጋገር፣ ለቤተሰብ የጨዋታን ጊዜ መመደብ እና የመሳሰሉት በመሀላችሁ ያለውን ፍቅር በማጠንከር በስራችሁ ላይም ስኬታማ እና ደስተኛ እንድትሆኑ ያግዛችኃል፡፡

 

      2. መደበኛ እቅድ ይኑራችሁ

ከስራ ወቶ ወደ ቤት መግባት፣ በምሳ ሰዐት ልጆችን በስልክ ማዋራት እና የመሳሰሉት አመዛዛኝ መንገዶች ናቸው፡፡ እንዲህ አይነት ዘዴዎች የስራ ጫናን በማቅለል እና ጭንቀትን በማስወገድ ይታወቃሉ፡፡ ቤተሰባችሁም በቀላሉ ስለ እናንተ የስራ እና የጤና ሁኔታ እንዲገነዘቡ ያደርጋል፡፡

እንዲህ አይነቱን ሂደት ለብቻችሁ ማቀድ አትችሉም፤ ከቤተሰባችሁ ጋር በመቀመጥ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ በዝርዝር ማስቀመጥ ከዛም የእያንዳንዳቸውን ፍላጎት ለማሟላት መጣር፡፡ ለምሳሌ፡- እናንተ ጠዋት ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት ማድረስ ካለባችሁ ከሰዐት ደግሞ አንዳችሁ መቀበል ይኖርባችኃል፡፡ የቤት ውስጥ የስራን ጫና መከፋፈል ፍቅርን መተሳሰብን እና አንድነትን እንድታጎለብቱ በማድረግ መልካም ቤተሰብ እና ስኬታማ ሰራተኛ መሆን ይቻላል፡፡

 

       3. አይሆንም ማለትን ተማሩ

አንድ ሠው በተደጋጋሚ እንድትሰሩላቸው የሚፈልጉትን የውለታ ስራ እና ትእዛዝ አልችልም ማለትን አስለምዱ፡፡ መልካምነት በጣም አስፈላጊ ቢሆንም እናንተን እና ቤተሰባችሁን በማይጎዳ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ዘመናዊነት ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ ለÕደኛችሁ ወይም ለስራ ባልደረባችሁ አዋቂ እና ፈጥኖ ደራሽ ከሁናችሁ ሁልጊዜም ለእነርሱ አንደኛ ሆናችሁ ትቆያላችሁ፡፡ እንዲሁም ልጆቻችሁ በሚያደርጉት የመጀመሪያ ድርጊት ሁሉ አብራችኃቸው ሁኑ በሚፈልÕችሁ ሰዐት ተገኙ ያን ጊዜ እርስ በእርስ መዋደድን እና መተሳሰርን ትፈጥራላችሁ፡፡ በቤት ውስጥ እና ከቤት ውጪ ያለባችሁን ሀላፊነት በአግባቡ እና በጊዜው ከተወጣችሁ ከምቶዱዋቸው ጋር ጥሩ እና በደስታ የተሞላ ጊዜን ለማሳለፍ ትታደላላችሁ፡፡

 

        4. ዘዴን እንጂ ጉልበትን ተጠቅማችሁ አትስሩ

በሳምንት ውስጥ ለቤተሰባችሁ መስጠት የሚገባችሁን ጊዜያት በማይረቡ ምክንያቶች እንዳባከናችኃቸው ሲገባችሁ ምን ይሰማችኃል? እነዛን አለአግባብ የጠፉ ጊዜያት ለቤተሰባችሁ ሰታችሁ ቢሆን ቤተሰባችሁን ደስተኛ ማድረግ በቻላችሁ ነበር፡፡

አስፈላጊውን ስራ በጊዜው ስታከናውኑ የምትተርፋችሁን ቁራጭ ጊዜ ከምቶዱዋቸው ጋር ለማሳለፍ እድል ታገኛላችሁ፡፡ የተሰጣችሁን የአመራር ስራ በሀላፊነት እና በጊዜው ስትወጡ በተመሳሳይ ደግሞ ቤት ውስጥ ያለውን የስራ ጫና በመተጋገዝ እና በየተራ ብትሰሩ የበለጠ ትርፋማ ትሆናላችሁ፡፡ ስራችሁን ለሌሎች ማሳየት እና እቅዳችሁን በግልፅ ማስቀመጥ ሀሳብን ለመጋራት እና ለመተጋገዝ ስለሚያስችል የስራን ጫና ማቅለል እና በጊዜው ማድረስ ይቻላል፡፡

 

        5. ለእራሳችሁ የሚሆን ጊዜ አውጡ

አብዛኛውን ጊዜ እቅድ ስታወጡ የቤተሰባችሁን ጊዜ በማይጋራ መልኩ ብቻ ነው አይደል? ግን መሆን የለበትም፤ ጥናቶች እንደገለፁት “የኔ ጊዜ” ብላችሁ የምታሳልፉዋቸው ጊዜያት አጠቃላይ የህይወት እርካታን በመጨመር በስራም አለም ላይ ከፍተኛ ምርታማነትን ታበለፅጋላችሁ፡፡ ትኩረትንም እንድትላበሱ በማድረግ ለብቻችሁ ጊዜያችሁን እንድታጣጥሙ እና የጊዜን ትርጉም እንድታውቁ ያግዛል፡፡ ጊዜያችሁን ፊልም በማየት እና በእንቅልፍ የምታሳልፉ ከሆነ እርካታን ትነፈጋላችሁ፡፡

 

እነዚህን ዘዴዎች ያለ ተጠያቂነት ስሜት ግልፅ ፍቃድ በመውሰድ ከምቶዱት ጋር ጊዜያችሁን በአግባቡ እንድታሳልፉ ያግዛሉ፡፡ ባላችሁ የኑሮ መጠን እና ጊዜም የምቶዱትን እና የሚያስደስታችሁን ነገሮች በማከናወን ጊዜያችሁን ማጣጣም ትችላላችሁ፡፡ ምቹ የሆነ የስራን እና የቤተሰብን ጊዜ አመዛዝኖ ተግባር ላይ ማዋል የማይቻል አይደለም ስለዚህ በጥንቃቄ በመተግበር ለራሳችሁ እና ለሚወዱዋችሁ እርካታን ፍጠሩ፡፡