Blog > Interview Tips

በቃለ መጠይቅ ጊዜ ሊጠየቁ የሚችሉ የተለመዱ ጥያቄዎች

ስራ ለመቀጠር ስትሄዱ ሊያጋጥሙአቹ የሚችሉ ብዙ አይነት ጥያቄዎች ይኖራሉ፡፡

ከነዛም ውስጥ ተዘጋጅታችሁባቸው ብትሄዱ ቃለ-መጠይቃችሁን ስኬታማ ያደርጋሉ ብለን ያሠብናቸዉን 10 ጥያቄዎች እናካፍላቹ፡፡

  1. እራሣችሁን ግለጹ?

ምንግዜም ስለራሣቹ ጠቅለል አድርጋቹ የመግለጽ ልምድ ሊኖራቹ ይገባል፡፡ ስለነበራቹ እና ስላሣለፋችሁት የትምህርት እና የስራ መረጃ ከመናገር ይልቅ ስለማንነታቹ እና ለስራው ስላላቹ ጉጉት ላይ ብታተኩሩ መልካም ነው፡፡ ጥያቄውን ለሚጠይቃቹ ግለሰብ እንደ ሀሣብ ተቀጣሪ ብቶኑ ለስራው ስለሚኖራቹ አዎንታዊ ገጽታ አሳዩ፡፡   

  1. ያላችሁን ጥንካሬ ግለጹ?

ታታሪ ሠራተኛ፣ችሎታ ያለው እና ትጉህ መሆናችሁን መናገር አስፈላጊ ላይሆን ይችላል ምክንያቱም ማንም ሠው ድክመቱን አያወራምና፡፡ በምትኩ ግን ስለሠራችሁት እና ስኬታማ ስለሆናቹበት፣ ብቃታችሁን ስላረጋገጣችሁበት እና ችሎታችሁን ስላሳያችሁበት ስራ እያነሣችሁ በራስ በመተመማመን መንፈስ ብትገልጹት ይመረጣል፡፡

  1. ድክመታችሁን ግለጹ?

በፍጹም ድክመት የለኝም እንዳትሉ! ይህ የሚያሳየው ለቃለ-መጠይቁ ዝግጁ እንዳልሆናቹ ነው፡፡ እንደዚሁም ጎበዝ ሠራተኛ ነኝም የሚል መልስ እንዳትሠጡ፡፡ ማስታወስ ያለባችሁ ድክመታችሁን ማወቅ መቻላቹ ጥንካሬያችሁን ያሳያል፡፡ ትኩረት ማድረግ የሚያስፈልገው ስራችሁን የተሻለ ማድረግ ስለሆነ ያላችሁን ድክመት በመናገር መፍትሄው ላይ ማተኮር ነው፡፡ ጥያቄውን የሚጠይቃችሁ ግለሰብ መረዳት የሚፈልገው ስለራሣችሁ ግልጽ መሆናችሁን እና ለመሻሻል ያላችሁን ፍላጎት ነው፡፡

 

  1. ለምን እናንተን ለመቅጠር የተፈለገ ይመስላችኃል?

ላመለከታችሁት ስራ ብቁ መሆናችሁን እርግጠኞች ከሆናችሁ በራስ በመተማመን ስሜት ማሳወቅ ትችላላችሁ ግን ሌላ ልክ እንደናንተ ቃለ መጠይቅ የሚያደርገው ሠው ከእናንተ መስፈርት ጋር ተመሣሣይ ወይም ብልጫ ያለው ሊሆን ይችላል፡፡ በእንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ላይ ስራውን የተሻለ ለማድረግ ምን እንደሚያስፈልግ ትኩረት አድርጉ፡፡ ምናልባት ያላችሁን ብቃት በስሱ በመጠቀም በስራው ውስጥ ካሉት ሠዎች ጋር መልካም ዑደት መፍጠር ሊጠበቅባችሁ ይችላል፡፡ ለአብነት ያክል፤ በቃለ-መጠይቃችሁ ላይ ብቁ እንዳልሆናቹ ሊነግሩዋቹ ቢፈልጉ እንኩዋን ተስፋ አትቁለጡ ለመማር እና ለመልመድ ፍላጎት እንዳላቹ አሣዩ፡፡

 

  1. ከአምስት ዐመት በኃላ እራሣችሁን የት ነው የምታዩት?

በዚህ ጊዜ ስለ ምኞታቹ እና አላማችሁ ለመናገር እድል ታገኛላችሁ፡፡ስለምትፈልጉት የስራ ድርሻም ብትናገሩ ተመራጭ ነው፡፡አለቆች ቆራጥ የሆነ ሠው ምርጫቸው ነው ስለዚህ ምኞታችሁን እና ለስኬት ያላችሁን ጉጉት ለመናገር ማፈር የለባችሁም፡፡

 

  1. ከእኛ ጋር ለመስራት ምን አነሳሳችሁ?

በዚህ ጊዜ ስለ ድርጅቱ በቂ ዳሠሣ እንዳደረጋቹ ለማስረዳት መንገድ ይከፍትላችኃል፡፡ ግን ባጋጣሚዎች ያገኛችኃቸውን ማንኛውንም በድርጅቱ ውስጥ ስላሉ ሠራተኞችም ሆነ ስለ ድርጅቱ አሉታዊ የሆነ ነገር ላለመናገር ጥረት አድርጉ፡፡ ልትናገሩዋቸው ከምትችሉዋቸው ነገሮች ዋና ዋናዎቹ፤ ድርጅቱ በተመረጠው የስራ ዘርፍ ያለውን አሰራር፣ ግልጽ የሆነ የስራ መዋቅር እና ዝነኝነቱን መግለጽ አለባቹ፡፡

 

 

  1. የምትጠብቁት የደሞዝ መጠን ምን ያህል ነው?

ለአንዳንድ ሠዎች ይህ ጥያቄ አለመግባባትን ሲፈጥር ለተቀሩት ግን አሳሳቢም አይደለም፡፡ እንደየሠው ማንነት ለክፍያ ያላቸው አመለካከት ይለያያል ግን ጥያቄውን በመግባባት እና በግልጽ ለማለፍ ሞክሩ፡፡ በተለይ ስለ አከፋፈሉ ሁኔታ እና ተያይዞ ስለሚመጡ ጥቅማጥቅሞች መነጋገር አለባቹ፡፡ ለቃለ-መጠይቁ ከመቅረባቹ በፊት ግን በሌላ ተመሣሣይ ድርጅት ውስጥ ስላለው የደሞዝ መጠን አውቃቹ እና አወዳድራቹ መቅረብ ይኖርባችኃል፡፡

 

  1. ስራውን ለመስራት ምን አነሳሳችሁ?

መነሳሳት ግላዊ የሆነ ነገር ነው ስለዚህ መልሳችሁ በምንም አይነት ሁኔታ የተሳሳተ ሊሆን አይችልም፡፡ለስኬት ካላቹ ፍላጎት ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል ወይ ደግሞ ለቤተሰባቹ አስፈላጊ ሆኖ አጊንታቹት ይሆናል እነዚህ ሁለት መልሶች ለተጠየቃችሁት ጥያቄ ተመራጮች ናቸው፡፡

 

  1. ጥሩ ቡድን ለመፍጠር ምን ማድረግ የስፈልጋል?

ብዙ ሠዎች በሚያቀርቡት ማስረጃ ላይ ስላላቸው ጥሩ የስራ ህብረት እና ያሳኩዋቸውን የቡድን ስራዎች ይገልጻሉ የተወሰኑት ደግሞ በቃለ-መጠይቁ ላይ ይናገራሉ፡፡ የምትሰሩት ስራ በብዛት ከብዙ ሠዎች ጋር ግንኙነት ይኖረዋል ያንን ግንኙነት እንዴት መፍጠር እንዳለባቹ እና በአንድነት ተጣምራቹ መስራት እንደሚስፈልግ በምሳሌ እያከላቹ ትናገራላቹ፡፡ ይህንን ጥያቄ በተገቢው መንገድ መመለሳቹ ለቡድን መሪነትም ሆነ ለምትመደቡበት የስራ ዘርፍ የሀላፊነት እጩ ውስጥ እንድትገቡ ያደርጋችኃል፡፡

  

  1. መጠየቅ የምትፈልጉት ጥያቄ ይኖራል?

ሁልጊዜም ያዘጋጃችሁት ቢያንስ አንድ ጥያቄ ሊኖር ይገባል! በዚ ጊዜ ያላችሁን ቅልጥፍና በመጠቀም ለስራቹ ልምምድ ማድረግ ነው፡፡ስለነበራችሁ ቃለ-መጠይቅ እና ስለ ስራው ያልተነሱ ጥያቄዎችን እያነሳቹ መወያየት ትችላላችሁ፡፡ ሲጠይቃችሁ የነበለውን ግለሰብ ያልገባችሁን እንዲያብራራላችሁ ማድረግም ይቻላል፡፡ይህም የሚጠቅመው ስራውን ለመቀጠር ብቻም ሳይሆን በሚገባም እያዳመጣችሁ እንደነበር ስለሚያሳይ ጥያቄውን በሚጠይቃችሁ ሠው ላይም ጥሩ ገጽታ መቅረጽ ትችላላችሁ፡፡

 

እነዚህን 10 ጥያቄዎች ብቻም ላይሆን ይችላል የምትጠየቁት ግን በብዛት የተለመዱ ናቸው ብለን ያሰብናቸውን አስቀምጠንላችኃል፡፡ ማስታወስ ያለባቹ ሁሉንም ጥያቄዎች የመመለስ ግዴታ አለባቹ የሚል ህግ አይኖርም ግላዊ ነው ብላችሁ የምታስቡዋቸውን ጥያቄዎች ማስወጣት ትችላላችሁ፡፡ምንግዜም ግን ወደ ቃለ-መጠይቅ ከመግባታችሁ በፊት ለእነዚህ 10 ጥያቄዎች ዝግጁ መሆን አለባችሁ፡፡

 

ሁልጊዜም መልሳችሁ ቀጥተኛ እና ግልጽ ከሆነ ያላችሁን ቆይታ መልካም በማድረግ የጠያቂውን ቀልብ መግዛት ትችላላችሁ፡፡  

                                                              

                                                                     መልካም ዕድል!

 

በተለያዩ  የስራ መደቦች ያወጡ ማስታወቅያዎችን ለመመልከት www.jobs.et

ይጎብኙ