Blog > Self Development

በስራ ላይ ያለውን ጫና ለማስቀረት የሚረዱ 5 መንገዶች

የስራ ጫናን ለማስቆም የሚጥሩ ሠራተኞች በስራቸው እና ባላቸው ቤተሰባዊ ህይወት ደስተኛ እና ጤናማ ናቸው፡፡  

ሠራተኛ እና የቡድን ስራ አባል ከሆናችሁ ያለጥርጥር የእነዚህ እሴቶች ልምድ ይኖራችኃል፡-   

  • ብቁ እንድቶኑ ቴክኖሎጂ ያግዛችኃል፤ ኢሜል ማድረግ፣ የፅሁፍ እና የድምፅ መልክቶችን መላላክ አብዛኛውን ጊዜያችሁን ይወስዳል ከዛም ስራችሁን መስራት ትጀምራላችሁ፡፡
  • ንግግርን እና ጥያቄን በአግባቡ ለመተግበር እንዴት መፈፀም እንዳለባችሁ ተኝታችሁ እንኳን ያሳስባችኃል፡፡
  • ለምትሰሩት ስራ ዋጋ አይሰጣችሁም፤ ጥሩ ሀሳብ ቢኖራችሁም ማንም ሠው ግድ አይሰጠውም፡፡
  • በቂ ደመወዝ ስለማይከፈላችሁ እዳችሁ ይጨምራል፡፡
  • በአግባቡ እንኳን ስቃችሁ አታውቁም፤ ለመጨረሻ ጊዜም የተደሰታችሁበት ቀን መቼ እንደሆነ አታስታውሱም፡፡

በስራ ቦታ ላይ ያለ ጫና ስቃይ የበዛበት ነው፡፡ በስራችን ላይ ስንጨነቅ በአብዛኛው በቀላሉ መረበሽን፣ መበሳጨትን እና ውድቀትን በማስከተል ስራችንን ያበላሸዋል፡፡ በዚህ አይነት አጋጣሚ ቁጥር የሌላቸው ሠራተኞች በየቀኑ እራሳቸውን ለማግኘት ይተጋሉ፡፡ ስራችሁ የሚፈጥርባችሁ ጭንቀት በግላዊ ህይወታችሁ ላይ ተፅዕኖ በመፍጠር ከትዳር አጋራችሁ፣ ከልጆቻችሁ እና ከÕደኞቻችሁ ጋር ያለውን ሰላም ያደፈርሳል፡፡ ከጊዜም በኃላ አካላዊ እና ስነ-አዕምሮአዊ ጤናን ማወኩ አይቀሬ ነው፡፡ የስራ ልምድን ለማግኘት ከአቅም በላይ በሆነ ጫና ሙሉ ጊዜያችንን ሰውተን እንሰራለን፡፡ ከስራ ጫና ጋር፤ ልጅ ማሳደግ፣ መስክ መውጣት፣ ለልጆች ጊዜ መስጠት፣ ከመመገብ እና ከመንከባከብ በስተጀርባ ብዙ እድሎች እንዲያመልጣችሁ ያደርጋል፡፡ ይህ አይነት ውጥረት ለልብ እና መሰል በሽታዎች ሊዳርግ ይችላል፡፡   

ጭንቀት በጤናችሁ ላይ ችግርን ሲያደርስ ልክ እንደ መንቂያ ደውል ልታስቡት ይገባል፡፡ በስራ ጫና ዙሪያ ብዙ ጥናቶች ተደርገዋል፤ ሠዎች ከተላመዱት በኃላ እንዴት ስኬታማ እነደሚሆኑ፣ ለውጥን እና መከራን መቋቋም እንደሚችሉ ይገነዘባሉ፡፡ ስለዚህ ሁላችሁም ጭንቀትን ለማጥፋት ቀላል መንገዶች መልመድ አለባችሁ፡፡ በጥልቀት ማሰብ፣ ረዥም ጉዞን ማድረግ እና ሌሎችን በተመስጦ ማዳመጥ መቻል ለችግራችሁ መፍትሄ መሆን ይችላል፡፡

አሉታዊነትን ማስቀረት ዋናው ነገር ሲሆን ከስራ ፈላጊዎች እና ከተገላጋዮች ጋር በየጊዜው ጭንቀታችሁን ማጋራት አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይ ለተቀጣሪ ሰራተኞች እና በቡድን ለሚሰሩ ሠዎች ላይ የሚከሰተውን ጫና ለማስቆም የሚረዱ 5 መፍትሄዎችን ተመልከቱ፡-

  1. ከአለቆች ጋር ቅርበት መፍጠር

የሁለት ቡድኖች ጠንካራ ግንኙነት በእምነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ንግግር ማድረግ የሚፈለግበት ዋናው ምክንያት የሁለቱም ቡድኖች በአንድ ግልፅ መስመር የግንኙነት ሁኔታ ለማዳበር ሲሆን ይህንን ለመፈፀም የሚረዳ ተቆጣጣሪው መንገድ እምነት ነው፡፡ ከአለቃችሁ ጋር የአንድ-ለአንድ ንግግር ስታደርጉ ልትገረሙ ትችላላችሁ፡፡ ሁልጊዜም ስታወሩ ከፍ ባለ ድምፅ ንቁ ሆናችሁ እና በጥሩ ስሜት ከሆነ ያሰራችሁን ጭንቀት በመፍታት ሀሳባችሁን በነፃነት በመግለፅ አላማችሁን ትገልፃላችሁ፡፡

 

       2. እርዳታ ጠይቁ

ከአለቃችሁ ጋር ጥሩ ቅርበት ቢኖራችሁም እንኳን የመደመጥ ስሜት እና ከእናንተ ምን እንደሚጠበቅ ማወቅ እና በአቀዳችሁት መንገድ ስራችሁ እንዲካሄድ ልትጨነቁ ትችላላችሁ፡፡ እርዳታ ባስፈለጋችሁ ሰአት ጠይቁ፤ መጠየቅ ምንም ችግር የለውም፡፡ ስትጠይቁ ታውቃላችሁ እርዳታንም ታገኛላችሁ፡፡

 

      3. ተባበሩ እንጂ አትወዳደሩ

የስነ-ልቦና ጥናቶች እንደገለፁት፤ ማህበራዊ ድጋፍ በተለየ መልኩ ለአካላዊ እና አዕምሮአዊ ጤና አስተዳደር አስፈላጊ ነው፡፡ በአጠቃላይ አዎንታዊነት የተላበሰ ማህበራዊ ድጋፍ መጨመር የጭንቀት ህመምን ለማስታገስ እና የስራ ጫናን በመቀነስ ቀዳሚነት ይይዛል፡፡ የስራ ባልደረባችሁን እንደ ተወዳዳሪ ካያችሁ ሁልጊዜም በጭንቀት እና በብስጭት ትሞላላችሁ፡፡ በአንፃሩ ከባልደረባችሁ ጋር በመቀመጥ እርስ በእርስ እንዴት መረዳዳት እንደምትችሉ መነጋገር ስራችሁ ቀልጣፋ እና አመርቂ ውጤት እንዲያመጣ ያግዛችኃል፡፡ እንደ ቡድን መስራት እና እርስ በእርስ መደጋገፍ በከፍተኛ ደረጃ ጫናን ያስወግዳል፡፡ ጊዜያችሁን ለስራ ባልደረቦቻችሁ ስትለግሱ በከፍተኛ ደረጃ የስራ ጫናን ታስወግዳላችሁ፡፡

 

     4. በቂ እንቅልፍ ተኙ

እንቅልፍ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በቀን ውስጥ የተወሰነ እንቅልፍ መተኛት ማስቀረት የማስታወስ ችግር፣ ድብርትን እና ሙድን ያበላሻል፡፡ በሳምንት ከ80 በላይ ሰዐቶችን የሚሰራ ድርጅት ውስጥ ከሆናችሁ አርፍዳችሁ ለመግባት ወይም ሲደክማችሁ በጊዜ ለመውጣት ማስፈቀድ ይኖርባችኃል፡፡ የእረፍት ጊዜ እንደሚስፈልጋችሁ አስረግጣችሁ መናገር ተገቢ ነው፡፡

 

   5. ትኩረት ማድረግ

ስራችሁን አከናውናችሁ ለመጨረስ ሰዐት መያዝ ካለባችሁ ያዙ፡፡ ትኩረት ያለው ስራ ምርታማነትን ይጨምራል፡፡ ስራን አከናውኖ በጊዜው መጨረስ ጥሩ ስሜትን ይሰጣል ጫናንም ያስወግዳል፡፡ ለሚቀጥለውን ስራ በኃይል እንድትሞሉ እና በአዲስ ጉልበት እንድትነሱ ያግዛል፡፡

በመጨረሻም አሉታዊ ፀባይን ለማሻሻል የተቻላችሁን አድርጉ፡፡ በማንኛውም አጋጣሚ የሠዎችን መልካምነት መመልከት የራሳችሁን ጤና፣ ስራችሁን እና ህይወታችሁን በአግባቡ ለመምራት ያግዛል፡፡