Blog > Self Development

ስራችሁን ለማሻሻል ስታስቡ ድክመታችሁ ላይ ሳይሆን ጥንካሬያችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ

በድክመታችሁ ላይ ሰርታችሁ ድንጋይ የተሸከማችሁ ያክል ስሜት ተሰምቷቹ አያውቅም? ምናልባት አሁን ያላችሁ ድክመት ምክንያትም እርሱ ይሆናል፡፡ አንድ Õደኛዬ በቅርብ እንዲህ አይነት ሁኔታ አጋጥሞት ነበር፤ ከተወሰኑ አመታት በፊት የአስተዳደር ቦታ ላይ ይሰራ ነበር፡፡ ባለው የአስተዳደራዊ ተግባር ላይም የሀላፊነት ቦታን ወስዶል ግን ያለው የስራ ተጽኖ የግል ሂወቱን አበላሸው፡፡ ከረዥም ጊዜ በኃላ፤ በቦታው ላይ ያለው ሚና ጥሩ እንዳልሆነ ተገነዘበ እናም ምንም ያህል በድካሙ ላይ ጠንክሮ ቢሰራ ስራው አመርቂ ውጤት እነደማያመጣ አወቀ፡፡

ለልማት ስንጥር ሁልጊዜም የእኛን እና የሠራተኞቻችንን ድክመት ለማስቀረት ወጥረን እንሰራለን፡፡ ለምን ይሄ የሚደረግ ይመስላችኃል? ከምክንያቶቹ መሀል አንደኛው አእምሮአችን ያለው “አሉታዊ አድሎ” ለማስቀረት ነው፡፡ አዎንታዊ ልምዶች ጭብጥ የሆነ እውቀትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስቀስሙናል ወይም ማስታወሻ ለማስቀመጥ አፋጣኝ ትውስታን ያላብሱናል፡፡ ይህ ተሞክሮ በግልጽ ተደራሽነት ያለው ሲሆን በተፈጥሮ ተÕዳኝ ድክመቶችን እና አሉታዊ ተሞክሮን ለማስወገድ ይረዳናል፡፡ ይህ የአሉታዊ ዝንባሌ በተለይ በአስተዳደር ላይ የተስተዋለ ሲሆን መሪዎች በሚያደርጉት የችግሮች ትኩረት ግምታዊ እንቅስቃሴ ላይ ነገሮች ከመስፋፋታቸው በፊት የማፈንገጥ ባህሪን ያሳያሉ፡፡    

ግን ችግሩ፤ ድክመታችንን ማወቅ እና ትኩረት ማድረግ ፍጻሜውን ለማሻሻል በቂ አይደለም ብለን ስለምናስብ ነው፡፡ በእርግጥ የድክመታችን ትክክለኛው ቦታ መታወቁ አይቀርም፤ ቅድሚያ አጎልባች በሆኑ ነገሮች ላይ ትኩረት ካደረግን ግን ጉልበታችንን በማዳከም ውስን ወደሆነ ውጤት ይመሩናል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ጥንካሬን መጠቀም መቻል በስራ ቦታ ላይም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች በምታከናውቸው እያንዳንዱ ነገር ፍጻሜውን ስኬታማ ያደርግላችኃል፡፡

ስለዚህ በልምምድ ብልጽግናን ለማግኘት ጥንካሬያችሁ እንዴት ነው የምትለኩት? በቅርብ ጊዜ በተደረገው ጥናት ጥንካሬ ላይ በማተኮር እራሳችሁን እና ቡድናችሁን ሊያበለጽግ የሚችል 4 ልምምዶችን አስቀምጠዋል፡-

  1. ጥንካሬዎቻችሁን በመለየት እንዴት አቀናጅታችሁ መስራት እነደምትችሉ ማወቅ፡-

ንጹህ ሀይል ወደ ማንኛውም አስፈላጊ ደረጃ ይመራል፤ በከፍተኛ ደረጃም ሲያድግ ይታያል፡፡ በጥንካሬያችሁ ላይ ትኩረት ስታደርጉ ስራችሁ ካለው ትልቅ አላማ ጋር ያስተሳስራችኃል በተጨማሪም ልዩ የሆነ አስተዋጾም ያደርጋል ይህም የወደፊት ግባችሁን ሂደት ለማሳካት በሀይል ይሞላችኃል፡፡ እ.ኤ.አ በ2008 የስራ ተነሳሽነት 30 በመቶ ዝቅ ብሎ ነበር፡፡ አዝማሚ ሂደቱን ለማስቀረት ጥንካሬያቸው እና ድክመታቸው ምን እንደሆነ የተጣራ ትኩረት ተደርጎ ነበር፡፡

ጉልበታችሁን እንዳሰባችሁ ለመቆየት ጥንካሬያችሁን ማወቅ እና ተነሳሽነታችሁ አስፈላጊ ነው፡፡ ከተደረጉት ብሁ ግምገማዎች መካከል ውስኖቹ ብቻ ናቸው ትክክለኛ እና ውጤታማ ሆኖ የተገኙት፤ ዋናው ነገር በግምገማው ወቅት የእናንተን ጥንካሬ እና መዋለንዋዩን ማግኘት ነው፡፡  

 

እነዚህ ግምገማዎች ጥሩ ጅምር ናቸው ግን በጥልቅ መመልከት ያስፈልጋል፡፡ ጥንካሬያችሁ እንዴት ከስራችሁ ጋር እንዳስተሳሰራችሁ እና መነሳሳትን እንዳሳደረባችሁ አስቡ፤ ከዛም በአንድ ዐረፍተ ነገር ለመገለጽ ሞክሩ ይህን በማድረጋችሁ የመስራት ጥንካሬያችሁ ጥልቅ የሆነ ሀይልን ያላብሳችኃል፡፡ አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ፡- የመገምገሚያ መሳሪያዎችን ድጋፍ ለማድረግ ብዙ ጊዜ እና ንብረት አውጥቻለው፤ ለዚህም የአቅሜን ለመፈጸም እና ተነሳሽነትን ለማበልጸግ ሰንሰለት ሰርቻለው ግን ሀሳቡን የተቀበለ ሠው አልነበረም ምክንያቱም የመበልጸግ ተነሳሽነት በቀጥተኛ መንገድ ለህዝቡ ባለመቅረቡ ነበር፡፡ ጥንካሬያችሁን ለማበልጸግ ስትሞክሩ መንገዶች ሲበላሽባችሁ እና ተነሳሽነታችሁ ሲጠፋ አላማችሁን ከግብ ለማድረስ በትጋት መስራት አለባችሁ፡፡

 

       2. ውስጣችሁ የሚፈጥረው “ለምን?” የሚል ጥያቄ መልስ መፈለግ፡-

ይህንን ተልእኮ የምታከናውኑት “ለምን?” የሚለውን ጥያቄ መመለስ ስትችሉ ነው፡፡ ለምንድነው ጠዋት የምትነሱት? እና ወዘተ…በየቀኑ ውስጣችሁ የሚጠይቃችሁን ለምን የሚል ጥያቄ መልስ ማወቅ አለባችሁ፡፡

 

ለሌሎች ጥቅም ብላችሁ በደመነፍስ የምታደርጉት ምንድነው? ለሠዎች ያለክፍያ ማድረግ የሚያስደስታችሁስ ምንድነው? በመቀጠል በእያንዳንዱ ዐረፍተ ነገር ላይ ለምን የሚል ቃል አስገቡበት፡፡ “የተፈጠርኩት…” ሁልጊዜም ይህንን አጣርታቹ ማወቅ አለባችሁ፡፡ ለምሳሌ፡- “እኔ የተፈጠርኩት የሠው ልጆች በሂወታቸው እና በስራቸው ላይ ያላቸውንን ትስስር ለማመቻቸት ነው” በሠዎች መካከል ያለው ትስስር በስራ ላይ እና በእለትተለት ኑሮ ላይ እንዴት አጣጥመው መሄድ እንዳለባቸው ማሳወቅ እወዳለው፡፡ በስራዬ ጥሩ እንደሆንኩም ተስፋ አደርጋለው እናም አላማዬ ስኬታማ እና ጤነኛ የሆነ ትስስር መፍጠር ስለሆነ ከምንም በላይ በስራዬ ደስተኛ ነኝ፡፡

 

ለምን ማለታችሁ የህይወታችሁ መሰረት ነው እናም አላማ አድርጋችሁ የምትነሱት በጥንካሬያችሁ ላይ ነው፡፡ ስለ ጥንካሬያችሁ በግልጽ ካወቃችሁ ለምን የሚለው ጥያቄ ጉልበታችሁን እና ተነሳሽነታችሁን በመጨመር አላማችሁን ከግብ እንድታደርሱ ይረዳችኃል፡፡

 

   3. በሚያበረታታ ግንኙነት ስርአተ-ምህዳሩ ማበልጸግ፡-

ከተደረጉት ጥናቶች መካከል በዋናነት በግንኙነት መካከል ያለውን ጥንካሬ ማበልጸግ ነበር፡፡ ስለ ጥንካሬያችሁ ካላችሁ ግንኙነት እና ነገሮችን በጭንቅላታችሁ ከማብላላት በላይ ገፍታችሁ መሄድ አለባችሁ፡፡ ሌሎች ሠዎች ሲረዶችሁ እና ጥንካሬያችሁን ሲያበለጽጉ ማየት ትፈልጋላችሁ፡፡ ስለእናንተ ጥንካሬ ሊያውቁ የሚችሉ ሠዎችን ጥንካሬያችሁን ሲያዩ ምን እንደሚያስቡ ጠይቸው፤ ብዙም ባይሆን የተወሰነ ነገር ሊያረጋግጡላችሁ ይችላሉ ወይም እናንተ ያላያችሁትን ጥንካሬ ሊገልጡላችሁ ይችላሉ፡፡ እራሳችሁን ማንቀሳቀስ መቻላችሁ ጥንካሬን ለማግኘት ድጋፍ ያለው ግንኙነት ላይ እንዲንጸባረቅ ያግዛል፡፡  

ቅድሚያ ችግሩን ለመፍታት ከመነሳት ይልቅ ሌሎች ጥንካሬያቸውን እንዲያበለጸጉ እንደረዳችኃቸው ውይይት እና ምርመራ እንዲያደርጉ መንገድ ክፈቱ፡፡

 

     4. ድክመታችሁን ወደ ጥንካሬ ለመቀየር ጥረት አድርጉ፡-

የጥንካሬ ምዘና የተጀመረው የሠዎች ድክመት ችላ መባል በመጀመሩ ነው፡፡ በዚህም ጥናት የተገኘው መረጃ የሠዎችን ድክመት ማወቅ መቻል ነበር፡፡ ድክመታቸው ወደኃላ ያስቀራቸው ሠዎች ጥንካሬያቸውን መፈለግ እንዲችሉ ጥለቶች ተደርገዋል፡፡ ለምሳሌ፡- አንድአንድ ጊዜ ድክመታችሁ የጥንካሬያችሁ ውጤት ይሆናል፡፡ የትኛው ድክመታችሁን ነው ለይታችሁ የምታውቁት? ምክንያቱም ለውጤታማነታችሁ መደራደር አስፈላጊ የሆነውን የብቁነት ተዛምዶ ልክ እንደ፤ ስሜትን መቆጣጠር ለረዥም ጊዜ ውጤታማ ሆኖ ለመቆየት ተመራጭ ነው፡፡

 

ስትናደዱ ሠዎች ላይ መጮህ ወይም አግባብ ያልሆነ ሰጣገባ ማድረግ ክልክል ነው እናም በእንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ጥንካሬያችሁን በመጠቀም ራሳችሁን መቆጣጠር ልምዳችሁ አድርጉ ግን ሌሎች ድክመቶች ላይ መስራት አለባችሁ ተብሎ የሚታሰበው ነገሮችን ጠልቆ ማወቅ እና ሀሳብን ማጋራት ናቸው፡፡

 

ድክመታችሁ ማንነታችሁን ሲጋርድባችሁ ጥንካሬያችሁን ተጠቅማችሁ እንዴት አላማችሁን በስኬት መተግበር የምትችሉበትን መንገድ መመልከት አለባችሁ፡፡ በእርግጥ የምትፈልጉት ነገር እናንተ ያላችሁበት ድረስ ላይመጣ ይችላል ግን ስራችሁን እየሰራችሁ ስኬታችሁን የምታበለጽጉበትን መንገድ መፈለግ ይኖርባችኃል፡፡ ሁሉም ሠው የጥንካሬ መሠረት አለው፤ ለመጠቀምም ልምምድ አድርጉ ያኔም አላማችሁን ለማሳካት አንድ ደረጃ ያወጣችኃል፡፡