Blog > Employers

ሠራተኞቻችሁ ድርጅታችሁን የማሳደግ አቅም እንዳላቸው ተገንዝባቹ ታውቃላችሁ?

በአለም ላይ ንግድ የሚለው ቃል ከፍተኛ ተወዳዳሪ ያለው ነው፤ እናም የሚፈለገው ካለው የገበያ ውድድር በላይ ሆኖ መገኘት መቻል ነው፡፡

አብዛኛው የንግድ ኢንዱስትሪ ፍላጎት አዲስ ምርት ማምረት እና የደንበኞቹን አገልግሎትማሻሻል ነው፤ ሁለቱንም ሀሳቦች ስኬታማ የሆነ ንግድን ለማስረጽ ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ ለዛም ነው ሠራተኞች ላይ ትኩረት ማድረግ የተፈለገው፡፡

በሠራተኞች ላይ የበለጠ ትኩረት ባደረጋቹ ቁጥር እና በድርጅቱ ውስጥ ደስተኛ ሆነው እንዲቆዩ መንገድ ካመቻቻቹ የንግዱ አቅም በአንድ አፍታ በአስደናቂ ሁኔታ ሲያድግ ታያላችሁ፤ያንግዜ ተወዳጅ፣ የተከበረ እና ስኬታማ የንግድ ባለቤት ትሆናላችሁ፡፡

ስኬታማ የንግድ ቁልፍ ማግኘት ከፈለጋችሁ ሁልጊዜም ሠራተኞቻችሁን ማበረታታት እና ብቁ ማድረግ አለባችሁ፡፡ በዋናነት፤ የንግድ ባለቤቶች ከሠራተኞቻቸው በስተጀርባ ናቸው፤ የደንበኞችን እርካታ የሚጠብቁት ከንግዱ በስተጀርባ የሚሆኑት እና የደንበኞችን ፍላጎት የሚያውቁት ሠራተኞች ናቸው፡፡

የተሰማራችሁበት የንግድ ስራ አመርቂ ውጤት እንዲያሳይ በሠራተኞቻችሁ ላይ ትኩረት የምትሰጡባቸውን 4 መንገዶች ተመልከቱ፡፡

 

1. ሠራተኞቻችሁ በድርጅታችሁ ውስጥ ምንያህል ዋጋ እንዳላቸው አሳዩዋቸው

 

ብዙ ድርጅቶች ከዚህ በተቃራኒው እንደሚያደርጉ እሙን ነው፡፡ሠራተኞቻቸውን የሚያይዋቸው በተሳሳተ መንገድ ነው፤ የሚያናግሯቸው እንኳን በቀላሉ በሌሎች ሠራተኞች ሊቀይሯቸው እንደሚችሉ እና ለድርጅታቸው መስራታቸውን እንደንቀት ይቆጥሩታል፡፡ሠራተኞችን አክብሮት ባለው መንገድ ማዋራት እና ወደፊት ያላቸውን ራዕይ ማሳየት ደስተኛ ሆነው እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡

ሠራተኞች ለደንበኞቻችሁ የሚያሳዩት ጸባይ ለሚኖራችሁ ስኬታማ ንግድ ትልቁ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜም ለሠራተኞቻችሁ እንደምታስቡላቸው አሳዩዋቸው፣ በየሁለት ሳምንቱ የድርጅቱን ሠራተኞች ሰብስባችሁ ምሳ ጋብዙዋቸው፣ ከቢሮ ውጪ በወር አንድ ጊዜ የወዳጅነት ጊዜያትን አሳልፉ፣ ግላዊ ችግር ሲያጋጥማችሁ ያለምንም ማንገራገር ፍቃድ ስጡዋቸው ያንጊዜ ለሚያስብላቸው እና ለሚጨነቅላቸው ሠው መስራት ያስደስታቸዋል፡፡

 

2. ሠራተኞቻችሁን ሊያነቃ የሚችል ማበረታቻ ፍጠሩ

 

አብዛኛው የንግድ ኢንዱስትሪ ማበረታቻ መፍጠር ያለው ጥቅም ከፍተኛ እንደሆነ ያምናል፤ አበረታች ክንውኖችን መፍጠር ሠራተኞችን ማነቃቃት እና ድጋፍ መስጠትም ነው፡፡ቢያንስ በሳምንት ወይም በወር ነጻ ምሳ ማቅረብ እና የገንዘብ ጉርሻ መስጠት አላማን ለማሳካት ቀላል መንገዶች ናቸው፡፡

 

ለወር ያቀዳችሁትን ግብ ለማሳካት አንድ የእረፍት ቀን ብትሰጡዋቸው እንኳን እናንተ እጥፍ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ ምክንያቱም በስራ ገበታ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ በአግባቡ መስራታቸው ለማይኖሩበት ቀን ማካካሻ መሆን ስለሚችል፡፡ለሠራተኞቻችሁ ማበረታቻ መስጠታችሁ በሚስሩት ስራ ስኬታማ እና ጎበዝ መሆናቸውን እንዲያምኑ ታደርጋላችሁ፡፡ይህም ከምንም በላይ ደስተኛ ያደርጋቸዋል፡፡

 

3. ድርጅቱ ያለውን አላማ ለሠራተኞቻችሁ አጋሩዋቸው

 

ብዙዎቻችሁ አስተውላችሁ ከሆነ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩም ሆነ ሌሎች ድርጅቶች ይህንን ሲተገብሩ አይስተዋልም፤ የሳምንት፣ የወር እና የዐመት ግባቸውን ለሠራተኞቻቸው አያጋሩዋቸውም፡፡ ይሄ በአብዛኛው ሠው አመለካከት ተቀባይነት የለውም፡፡

አላማን ለሠራተኞች ማካፈል ዋና ቁልፍ ነው፡፡ይህም ሁሉም ሠራተኞች አንድ አይነት ምልከታ እንዲኖራቸው እና የሹመት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የድርጅቱ አካል መሆናቸውን መገንዘብ ያስችላቸዋል፡፡ሁሉም ሠው በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ መካተት ይፈልጋል እናም ሠራተኞች ምቾት እንዲሰማቸው ማድረግ፣ ግብን ማሳወቅ እና ግቡን ለማሳካት ምንያህል እንደምትፈልጓቸው እና እንደምትተማመኑባቸው መናገር ከእናንተ ይጠበቃል፡፡

 

4. የሠራተኞቻችሁን ሀሳብ ተቀበሉ

 

ብዙ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሠዎች የሠራተኞቻችሁን ሀሳብ ሲቀበሉ አይስተዋልም፡፡አብዛኞቹ የንግድ ባለቤቶች ሚያስቡት ለንግዱ ኢንዱስትሪ የሚያስፈልገውን ሁሉ እንደሚያውቁ እና ያላቸው ሀሳብ ከሠራተኞች እንደሚበልጥ እና በቂ እንደሆነ ነው፡፡እንዲህ አይነቱ የተሳሳተ ሀሳብ ኢንዱስትሪውን ሲጥል እንጂ ሲያበረታታ አልተመለከትንም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሠራተኞች የተሻለ ሀሳብ አላቸው ምክንያቱም የደንበኞችን አስተያየት እና ቅሬታ በደንብ የሚያውቁት እነርሱ ስለሆኑ፡፡

 

ከሠራተኞች አዲስ ሀሳብ መቀበል ለንግዱ ኢንዱስትሪ ትልቁን ሚና መጫወት ሲችል ሠራተኞቹም በሚሰሩት ስራ ተደማጭነት እንዳላቸው እና የኔ ብለው እንዲያስቡ መንገድ ይከፍታል፡፡ የሠራተኞችን ሀሳብ በመቀበል እና በመመርመር የወደፊት የድርጅታችሁን ጥሩ ራዕይ ማካበት ትችላላችሁ፤ ያቀረቡትን ሀሳብ እንደተቀበላችኃቸውም ሲያውቁ ጉልበት በማግኘት ሀሳቡን ወደ ድርጊት ለመፈጸም በጋራ ይነሳሉ፡፡


ንግዳችሁን የምታሳድጉበት መንገድ በጣም ቀላል እና ብዙ ነው፡፡ግን ለሠራተኞቻችሁ ያላችሁን የተሳሳተ አመለካከት መቀየር በምትኩ ደግሞ ማበረታታት እና ንግዱን እንዲያሳኩላችሁ እድል መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ማስተዋል ያለባቹ ትልቁ ነገር ግን የሠራተኞች ጸባይ በቀጣሪዎቻቸው ጸባይ ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ሠራተኞቻችሁን ከደንበኞቻችሁ በተሻለ መልኩ ተንከባከቧቸው ያንጊዜ ሠራተኞቻችሁ የደንበኞቻችሁን እርካታ መጠበቁን ያረጋግጡላችኃል፡፡