Blog > Self Development

ማህበራዊ ህይወት ለስኬታማነት ቁልፍ መንገድ እንደሆነ ታውቃላችሁ?

ለሠዎች ዋጋ የምትሰጡበት መንገድ እና ሠዎች ለናንተ የሚሰጡት ዋጋ እኩል መለካት አይችልም፡፡ ነገርግን የእያንዳንዱን ሠው ልዩነት በቀላሉ እንድታውቁ ያስችላል፡፡ አብዛኞቹ ስራ-ፈጣሪዎች የሚያምኑት፤ ብዙ ጊዜያቸውን ከሚያሳልፉት ሠው ጋር ማንነታቸው ተወስኖ እና ተቆጥቦ እንደሚቀር ነው፡፡ በአቅራቢያችሁ ካሉ ሠዎች ጋር ሁልጊዜም ተስማምታችሁ እና ተግባብታችሁ መኖር ይከብድ ይሆናል ግን የኑሮ ልምድን፣ ሀሳቦችን፣ ድርጊቶችን እና ችሎታዎችን ትለዋወጣላችሁ፡፡ እራሳችንን በጠንካራ ሠራተኞች መካከል ካገኘነው እኛም ጠንካራ የማንሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡

አብረዋችሁ የሚሆኑ ሰዎች ያለጥርጥር ከእናንተ መውሰድ(እንደናንተ መሆንን) ይሻሉ፡፡ ጎበዝ እና ጠንካራ ሰራተኛ ከሆናችሁ መቼም ከአጠገባችሁ አይርቁም፡፡ ቅርበታችሁ ደግሞ ፈልጋችሁትም ሆነ በአጋጣሚ አንዳችሁ ከሌላችሁ እንድትማማሩ ያደርጋል፡፡ የምንኖርበት አካባቢ ወይም ሀገር ማንነታችን ላይ ትልቅ ተፅዕኖን ይፈጥራል እንዲሁም ስኬታማ ሠዎችን ብዙ ባወቅን ቁጥር ወደ ስኬት ጎዳና ለመÕዝ እራሳችንን ዝግጁ እናደርጋለን፡፡

ማህበራዊ ህይወት ማለት የእናንተ ዋጋ ነው፤ በተለይ ለስራ-ፈጣሪዎች ሁሉነገር ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ ማህበራዊ ህይወት ማለት አንድ ሠው ከአንዱ ይበልጣል ያንሳል ማለት ሳይሆን፤ በተቃራኒው ግን የእናንተን ዋጋ ለአለም ማሳየት ነው፡፡ የራሳችሁን ማህበራዊ ግንኙነት በመፍጠር ወደ ስኬታማ ስራ-ፈጣሪዎች ህብረት ውስጥ መቀላቀል ትችላላችሁ፡፡

  1. የራስን ምርት ማምረት

ስራ-ፈጣሪዎች የራስ ምርት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ይረዳሉ ግን እኛ ብዙ ምርቶችን ማዘጋጀት እና ለገበያ ማቅረብ እንችላለን፡፡ ሁሉም ሠው የራሱ የሆነውን ምርት ታዋቂ ማድረግ ይችላል ነገርግን ተፅዕኖ መፍጠሩ አይቀሬ ነው፡፡ ሠዎች የሚያውቁዋችሁ ጊዜያችሁን ከስኬታማ እና ሀብታም ሠው ጋር እንደምታሳልፉ ከሆነ ለእናንተ እና ለምርታችሁ የሚሰጡት ግምት ከፋተኛ ይሆናል፡፡ ጊዜያችሁን ከስራ-ፈጣሪዎች ጋር ካሳለፋችሁ የተለየ ሊያደርጋችሁ የሚያሥችል እውቅናን ታገኛላችሁ፡፡

 

  1. በአካባቢያችሁ ያለ ተፅዕኖ መመልከት

በአካባቢያችሁ ያለው ተፅዕኖ ማህበራዊ ህይወታችሁን ጤናማ አድርጎ ለማቆየት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ በጠንካራ ማህበረሰቦች መካከል ለመገኘት መጣር የሚጠበቀው ትልቁ ኃላፊነት የእናንተ ነው፤ ያንጊዜ ሠዎች ለራሳችሁ የምትጡትን ዋጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት ትልቅ ቦታ ይሰጡዋችኃል፡፡ ከሠዎች ጋር ያላችሁ ግንኙነት ለማስፋት ከፈለጋችሁ ወደ እናንተ እስኪመጡ አትጠብsቸው፤ የምትፈልጉትን እስክታገኙ ድረስ መታገል ያለባባሁን ያህል ታገሉ፡፡ እስኪ አሁን በሠዎች ዘንድ ስላላችሁ ዋጋ አስቡ፤ የስራ-ፈጣሪ የኑሮ ዘዴ ከምንም የመነጨ አይደለም፤ ለማደግ መስራት እንዳለባቸው ያምናሉ፤ መክፈል ያለባቸው ትልቅ ዋጋም ቢኖር ወደኃላ አይሉም፡፡ እራሳችሁን በግል አሳድጉና ከሌሎች የለያችሁን ምክንያት ተመልከቱ ከዛም ልዩነቱ ምን ያህል እንደሆነ ትረዳላችሁ፡፡

 

  1. ቀጣዩን እርምጃ መውሰድ

ማህበራዊ ህይወት በአካባቢያችሁ ተፅዕኖ ምክንያት የሚቆም አይደለም ግን ከጊዜ ወደጊዜ እየተቀየረ ይመጣል፤ በዚህም ሂደት ውስጥ ያላችሁ ዋጋ እየሰፋ እና እያደገ ይመጣል፡፡ በተመሳሳይ ሰዐት የአካባቢያችሁ ተፅዕኖ ልክ ማህበራዊ ህይወታችሁን ስትቀይሩ እንደነበረው ቀላል አይሆንም፡፡ እንደ ስራ-ፈጣሪ እናንተ ከምታsቸው ሠዎች የተሻላችሁ እንደሆናችሁ ታስባላችሁ፤ ሌሎች ምን አይነት ስራ እንደሰራችሁ ፣ ምን አይነት ዋጋ እንደከፈላችሁ እና እነርሱን እንዴት ማገዝ እንደምትችሉ ማወቅ ይፈልጋል፡፡