Blog > Self Development

ሙዚቃ ማዳመጣችሁ በስራችሁ ላይ ውጤታማ ሊያረጋችሁ የሚችልባቸው 12 መንገዶች

አንድ አንድ ጊዜ የሰዐታችሁን ደቂቃ ሲዞር መመልከት ወይም የስራ ባልደረባችሁ በስልኩ ድምፅ አልባ መልእክት ሲላላክ ትኩር ብላችሁ ማየታችሁን ታዝባችሁት አታውቁም? በቢሮ ውስጥ በየቀኑ የሚከሰተውን የድብርት ጊዜያት ለማስወገድ የሚረዳ የተሻለው መፍትሄ ሙዚቃ ነው፡፡

ሙዚቃ “የሀሳብ መዐበል” ውስጥ እንድትገቡ ይረዳል፡፡ ሌላው ቢቀር የምቶዱት ቅኝት በጆሩዋችሁ ሲደርስ የማይታለፉ የሚመስሉ ተደጋጋሚ ድርጊቶች ወይም የህይወት ፈተናዎች ይቀላሉ፡፡ በዛላይ አይናችሁ ሰዐታችሁን ማያ ጊዜ አይኖረውም፡፡

ስራችሁን ማፋጠን ከፈለጋችሁ ወይም የስራ ባልደረባችሁን መቅደም ካሰባችሁ ሙዚቃ ለውጤታማነታችሁ ምክንያት መሆን ብቻም ሳይሆን የበለጠ ተግባቢ እንድቶኑ ማድረግ ይችላል፡፡ ግን ምንግዜም እናንተ ጋር ያለው ድምፅ ሌላውን እንደማይረብሽ እርግጠኞች መሆን አለባችሁ፡፡  

(ለሽያጭ ሰራተኞች እና የደንበኞች አገልግሎት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች የስራው አይነት በስራ ላይ ባሉበት ወቅት ሙዚቃን እንዲያዳምጡ የሚፈቅድ አይደለም።  ከታች የምናነሳቸው ነጥቦችም ተመሳሳይ ስራ ለሚሰሩ ሰራተኞች የሚመከር አይደለም )

በስራ ቦታ ላይ ሙዚቃ ማዳመጥ የበለጠ ውጤታማ እንድቶኑ ያግዛል፡፡ ሙዚቃ በሰውነታችሁ ውስጥ ሲፈስ ፈጣን፣ ከጭንቀት ነፃ፣ ችሎታን፣ ትኩረትን እና ደስታን እንድትጎናፀፉ ያግዛል፡፡ የበለጠ ደግሞ ከታች የተዘረዘሩትን በጣም አስፈልጊ የሆኑት 12  የሙዚቃ ጥቅሞችን ተመልከቱ፡፡

  1. በአስቸኳይ ሙድን ማስተካከል

የሙዚቃ ዋናው ጥቅም በቶሎ ሙድን ማስተካከል መቻሉ ነው፤ በርካታ ሳይንሳዊ ማስረጃዎችም ይህንን ይመሰክራሉ፡፡ ሙዚቃ ስታዳምጡ የደስተኛነት ስሜትንም ያላብሳችኃል፡፡

      2. ተደጋጋሚ የስራ ክንውኖችን እንዳትሰለቹዋቸው ያደርጋል

በስራ መደጋገም ምክንያት የሚደርሰውን መማሰን በማስቀረት የበለጠ ስራችሁን እንድቶዱት እና እንድትዝናኑበት ያደርጋል፡፡

      3. በሀሳብ ማዕበል ያስዋኛችኃል  

በአብዛኛው የሀሳብ ማዕበል የሚከሰተው ስራችሁን በአግባቡ መከወን ስትችሉ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በተለይ ትክክለኛውን ሙዚቃ ከመረጣችሁ ሀሳባችሁን ብሩህ ያደርግላችኃል፡፡

     4. የስራ ፍጥነትን ይጨምራል

ምን አይነት ሙዚቃ ያዝናናችኃል? የትኛውስ መንፈሳችሁን ያድሳል? የመረጣችሁትን ከፍታችሁ ደጋግማችሁ ማዳመጥ ንቁ ሆናችሁ ስራችሁን እንድታቀላጥፉ ያደርጋል፡፡

     5. መረበሽን ያስወግዳል

በስራ ላይ መረበሽ ጥፋትን ያስከስታል፡፡ ሙዚቃን ስታዳምጡ ግን ትኩረት አድርጋችሁ እንድትሰሩ በማገዝ ያለ እንከን ስራችሁን እንድትጨርሱ መንገድ ይከፍታል፡፡

     6. የስራ ባልደረባን ለመሸሽ ያግዛል

መቼም ሁሉም ሠው የስራ ባልደረባውን ይወዳል ግን ቤተሰባችሁም ቢሆን በስራ ሰዐት እንዲረብሹዋችሁ አትፈቅዱም ታዲያ በዛን ጊዜ ሙዚቃ መፍትሄ ይሆናችኃል፡፡

    7. ፀጥታ የሰፈነበት ድርጅትን ለመምራት

ሁሉም የስራ ቦታዎች በጩኸት የተሞሉ አይደሉም፡፡ አነስተኛ ፀጥታ የሰፈነባቸው ድርጅቶች ግን በከፍተኛ ደረጃ ውጤታሞች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ሙዚቃ ደግሞ የድርጅታችሁን ድባብ ይለውጣል ስለዚህ በዝቅተኛ ድምፅ ስራችሁን ማከናወን ትችላላችሁ፡፡

     8. የተደበቀ የፈጠራ ችሎታን ያወጣል

እኛ ሠዎች እንጂ ማሽን አይደለንም፡፡ እያንዳንዳችን የፈጠራ ችሎታን ታድለናል፤ ሙዚቃ ደግሞ ችሎታችንን እንድናዳብር ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡

     9. እንድትንቀሳቀሱ ያደርጋል

ቢሮዋችሁ ውስጥ ያለው መቀመጫ ወንበር የመርገቡ ምክንያት ለዥም ጊዜያችሁን በመቀመጥ ስለምታሳልፉ ነው ስለዚህ በሚኖራችሁ ጥቂት ደቂቃዎች ሙዚቃ ከፍታችሁ እንቅስቃሴ ብታደርጉ መነቃቃት ያድርባችኃል፡፡

    10. “አትረብሹኝ!” የሚል ምልክትን ይገልፃል

የሙዚቃ ማጫወቻችሁን በጆሮዋችሁ ላይ ስትሰኩ ስራ እየሰራችሁ እንደሆነ እና ማንም እንዲረብሻችሁ ፍቃደኛ አለመሆናችሁን በግልፅ ስለሚናገር ያለ ምንም ረብሻ ስራችሁን ታከናውናላችሁ ማለት ነው፡፡

    11. የበለጠ ማህበራዊ ያደርጋችኃል

የሙዚቃ ማጫወቻችሁን በጆሮዋችሁ ላይ ስትሰኩ ስራ እየሰራችሁ እንደሆነ ይታወቃል ግን ባወለቃችሁት ሰዐት የስራ ባልደረቦቻችሁን ማዋራት እና ለእነርሱ ጊዜ መስጠት ያስችላችኃል ይህም የበለጠ መቀራረብን ይፈጥራል፡፡

    12. ሰዐት ማየት እንድታቆሙ ያደርጋል

በየደቂቃው ሰዐታችሁን ማየት በጣም አስጊ ሁኔታ ውስጥ ይከታችኃል፡፡ ሙዚቃ ደግሞ ሀሳባችሁን እንድትሰበስቡ እና በስራችሁ ላይ እንድታተኩሩ በማድረግ በጊዜ እንድትጨርሱ ያግዛችኃል፡፡