Blog

Blog Categories

ለሠዎች ዋጋ የምትሰጡበት መንገድ እና ሠዎች ለናንተ የሚሰጡት ዋጋ እኩል መለካት አይችልም፡፡ ነገርግን የእያንዳንዱን ሠው ልዩነት በቀላሉ እንድታውቁ ያስችላል፡፡ አብዛኞቹ ስራ-ፈጣሪዎች የሚያምኑት፤ ብዙ ጊዜያቸውን ከሚያሳልፉት ሠው ጋር ማንነታቸው ተወስኖ እና ተቆጥቦ እንደሚቀር ነው፡፡ በአቅራቢያችሁ ካሉ ሠዎች ጋር ሁልጊዜም ተስማምታችሁ እና ተግባብታችሁ መኖር ይከብድ ይሆናል ግን የኑሮ ልምድን፣ ሀሳቦችን፣ ድርጊቶችን እና ችሎታዎችን ትለዋወጣላችሁ፡፡ እራሳችንን በጠንካራ ሠራተኞች መካከል ካገኘነው እኛም ጠንካራ የማንሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ አብረዋችሁ የሚሆኑ ሰዎች ያለጥርጥር ከእናንተ መውሰድ(እንደናንተ መሆንን) ይሻሉ፡፡ ጎበዝ እና ጠንካራ ሰራተኛ ከሆናችሁ መቼም ከአጠገባችሁ...
አብዛኞቹ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የድርጅታቸውን ባህል የማሳደግ ድክመት ይስተዋልባቸዋል፡፡ በተለይ በአሁን ጊዜ አጥጋቢ ባልሆነው የደንበኛ እና የሠራተኛ ፍሰት ተወዳዳሪ ሆኖ መቆየት ከባድ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ ህዝቦች ከደንበኞች ጋር ቅርበት እንዲፈጥሩ ማድረግ፣ ገበያውን ማጥናት እና ውሳኔ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ አንድ መፅሀፍ ላይ የሰፈረው መግለጫ ምን ይላል፤ ስኬታማ ድርጅቶች ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት የደንበኞቻቸውን ስሜት በማዳመጥ፣ የዝንባሌን ባህል የማዳበር ግንባታ እና አስተዳደር ላይ ሲሆን ቡድናቸው ውሳኔዎችን መወሰን እንዲችሉ እና አዲስ ምርቶች በቋሚነት ማምረት እንዲችሉ ማድረግ ነው፡፡ 7 መደገፍ ያለብን የባህል ባህሪያት እንመልከት፡-    1....
ስኬታማ ለመሆን ውጤታማነት ለምን በጣም አስፈላጊ ይሆናል? ምክንያቱም በእያንዳንዱ የውሳኔያችሁ ሂደት ላይ ውጤታማነታችሁ ዋናውን ሚና ይጫወታል፡፡ ውጤታማ መሆናችሁ ምኞታችሁን ለማሳካት ይጠቅማችኃል፡፡ አብዛኞቹ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች በውጤታማነት የተካኑ ናቸው ምክንያቱም በብልጠት ስለሚሰሩ፣ አላስፈላጊ ጥረትን ስለሚያስቀሩ እና ጊዜያቸውን ስለማያባክኑ ነው፡፡ ፅኑ አ ቋ ም ከሌለ እና በአጋጣሚዎች ስኬታማነትን ማግኘት አይቻልም፡፡ አብዛኞቹ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች በቀላሉ አይወድቁም ወይም በውሳኔያቸው ሂደት ላይ መዝረክረክ አይታይባቸውም ምክንያቱም ከውሳኔያቸው በፊት ግባቸውን በጥልቅ የመመልከት፣ የማዋቀር እና ሙሉ በሙሉ የመዘጋጀት ልምድ ስላላቸው፡፡    እነዚህን ውጤታማ ስራ...
አንድ አንድ ጊዜ የሰዐታችሁን ደቂቃ ሲዞር መመልከት ወይም የስራ ባልደረባችሁ በስልኩ ድምፅ አልባ መልእክት ሲላላክ ትኩር ብላችሁ ማየታችሁን ታዝባችሁት አታውቁም? በቢሮ ውስጥ በየቀኑ የሚከሰተውን የድብርት ጊዜያት ለማስወገድ የሚረዳ የተሻለው መፍትሄ ሙዚቃ ነው፡፡ ሙዚቃ “የሀሳብ መዐበል” ውስጥ እንድትገቡ ይረዳል፡፡ ሌላው ቢቀር የምቶዱት ቅኝት በጆሩዋችሁ ሲደርስ የማይታለፉ የሚመስሉ ተደጋጋሚ ድርጊቶች ወይም የህይወት ፈተናዎች ይቀላሉ፡፡ በዛላይ አይናችሁ ሰዐታችሁን ማያ ጊዜ አይኖረውም፡፡ ስራችሁን ማፋጠን ከፈለጋችሁ ወይም የስራ ባልደረባችሁን መቅደም ካሰባችሁ ሙዚቃ ለውጤታማነታችሁ ምክንያት መሆን ብቻም ሳይሆን የበለጠ ተግባቢ እንድቶኑ ማድረግ ይችላል፡፡ ግን...
ቤተሰብን እና ስራን አመዛዝኖ ማስኬድ ከባድ ቢሆንም ግን ጊዜያችሁን ባግባቡ ከተጠቀማችሁ ሁሉም ቀላል ይሆናል፡፡ እነዚህን 5 እቅዶችንም በማውጣት እንዴት አጣጥማችሁ መ Õ ዝ እንዳለባችሁ ለማወቅ ያግዛል፡፡   ከእቅዶቻችሁ መካከል የቤተሰብ ጊዜን መስርቱ አብዛኛውን ጊዜ ከ3 እስከ 11 ሰዐት በስራ ገበታ ላይ ታሳልፋላችሁ፤ ታዲያ ለቤተሰባችሁ የምትሰጡት ጊዜ በየትኛው ሰዐት ነው? የራሳቸውን ስራ የሚሰሩ ብዙሀኑ ህብረተሰብ ስራቸው አልቆ ከቤተሰባቸው ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ ይናፍቃሉ፡፡ ይህንንም ለመተግበር ቀላል የሚሆነው በቀን ውስጥ ያላችሁን ስራ ባግባቡ እና በጊዜው መፈፀም ስትችሉ ነው፡፡ ለቤተሰባችሁ በቂ ጊዜ የማትሰጡ ከሆነ ህይወት...
የስራ ጫናን ለማስቆም የሚጥሩ ሠራተኞች በስራቸው እና ባላቸው ቤተሰባዊ ህይወት ደስተኛ እና ጤናማ ናቸው፡፡   ሠራተኛ እና የቡድን ስራ አባል ከሆናችሁ ያለጥርጥር የእነዚህ እሴቶች ልምድ ይኖራችኃል፡-    ብቁ እንድቶኑ ቴክኖሎጂ ያግዛችኃል፤ ኢሜል ማድረግ፣ የፅሁፍ እና የድምፅ መልክቶችን መላላክ አብዛኛውን ጊዜያችሁን ይወስዳል ከዛም ስራችሁን መስራት ትጀምራላችሁ፡፡ ንግግርን እና ጥያቄን በአግባቡ ለመተግበር እንዴት መፈፀም እንዳለባችሁ ተኝታችሁ እንኳን ያሳስባችኃል፡፡ ለምትሰሩት ስራ ዋጋ አይሰጣችሁም፤ ጥሩ ሀሳብ ቢኖራችሁም ማንም ሠው ግድ አይሰጠውም፡፡ በቂ ደመወዝ ስለማይከፈላችሁ እዳችሁ ይጨምራል፡፡ በአግባቡ እንኳን...
በድክመታችሁ ላይ ሰርታችሁ ድንጋይ የተሸከማችሁ ያክል ስሜት ተሰምቷቹ አያውቅም? ምናልባት አሁን ያላችሁ ድክመት ምክንያትም እርሱ ይሆናል፡፡ አንድ Õ ደኛዬ በቅርብ እንዲህ አይነት ሁኔታ አጋጥሞት ነበር፤ ከተወሰኑ አመታት በፊት የአስተዳደር ቦታ ላይ ይሰራ ነበር፡፡ ባለው የአስተዳደራዊ ተግባር ላይም የሀላፊነት ቦታን ወስዶል ግን ያለው የስራ ተጽኖ የግል ሂወቱን አበላሸው፡፡ ከረዥም ጊዜ በኃላ፤ በቦታው ላይ ያለው ሚና ጥሩ እንዳልሆነ ተገነዘበ እናም ምንም ያህል በድካሙ ላይ ጠንክሮ ቢሰራ ስራው አመርቂ ውጤት እነደማያመጣ አወቀ፡፡ ለልማት ስንጥር ሁልጊዜም የእኛን እና የሠራተኞቻችንን ድክመት ለማስቀረት ወጥረን እንሰራለን፡፡ ለምን ይሄ የሚደረግ ይመስላችኃል? ከምክንያቶቹ...
እራሳችሁን ተከታይ አድርጋችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ሁልጊዜም መሪ ለመሆንስ ፍላጎት አድሮባችሁ ያውቃል? ተከታይነት እና መሪነትስ በምንድነው የሚለያዩት? መሪነት ከተጨማሪ ሀላፊነት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ነው ግን ተጨማሪ እድሎችን፣ ተጨማሪ ክብርን እና ካቅማችሁ በላይ የሆን ቁጥጥር ይዞ ይመጣል፡፡ አንዳንድ ሠዎች መሪነትን ይሸሻሉ፤ እንደያስፈላጊነቱ በትልልቅ ቦታዎች ላይ ማገልገል ከባድ ሲሆንባቸው የተቀሩት ህይወታቸው እና እጣፈንታቸው እንዲቀየር እድገትን ይመኛሉ፡፡ ግን ያላችሁን ህይወት ተቀብላችሁ ትኖሩ ከነበረ እና በስራ መስካችሁ ላይ እንደ ተከታይ ካሳለፋችሁ መሪ ለመሆን ይቻላችኃል?   እንዴት መሪ መሆን ይቻላል? መሪዎች ልክ እነደማንኛውም ሠው ተወልደው እንጂ...
ብዙ ሰዎች ህልማቸው የሆነውን የራሳቸው ስራ ለመጀመር ተግተው ይሰራሉ፡፡ አብዛኞቹ ስኬታማ ስራ ፈጣሪዎች አሁን ያሉበት ስኬታማ ቦታ ለመድረስ የነበራቸውን ስራ በአግባቡ እና በትጋት ይሰሩ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት የስኬት መንገድ ላይ ለመድረስ ግን ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ አይሆኑም በተለይ ስራቸው የማያስደስታቸው ከሆነ ብዙ ጭንቀት እና አስቸጋሪ ጊዜያቶችን ያሳልፋሉ፡፡ ምኞት በጣም አስፈላጊ ነው፤ ሁልጊዜም ግን ወደፊት ለመጓዝ ምኞት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ያላችሁን ተነሳሽነት ለመምራት እና ከተቀጣሪ ወደ ስራ ፈጣሪ በጊዜው ለመድረስ እንደግብ ማስቀመጥ አለባቹ፡፡ አቅጣጫን መለወጥ ከባድ እና በሂደቱ ላይ ተስፋ መቁረጥ የተለመደ ነው፡፡ አሁን ያላችሁ ስራ ወደፊት አንድ እርምጃ...
በአለም ላይ ንግድ የሚለው ቃል ከፍተኛ ተወዳዳሪ ያለው ነው፤ እናም የሚፈለገው ካለው የገበያ ውድድር በላይ ሆኖ መገኘት መቻል ነው፡፡ አብዛኛው የንግድ ኢንዱስትሪ ፍላጎት አዲስ ምርት ማምረት እና የደንበኞቹን አገልግሎትማሻሻል ነው፤ ሁለቱንም ሀሳቦች ስኬታማ የሆነ ንግድን ለማስረጽ ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ ለዛም ነው ሠራተኞች ላይ ትኩረት ማድረግ የተፈለገው፡፡ በሠራተኞች ላይ የበለጠ ትኩረት ባደረጋቹ ቁጥር እና በድርጅቱ ውስጥ ደስተኛ ሆነው እንዲቆዩ መንገድ ካመቻቻቹ የንግዱ አቅም በአንድ አፍታ በአስደናቂ ሁኔታ ሲያድግ ታያላችሁ፤ያንግዜ ተወዳጅ፣ የተከበረ እና ስኬታማ የንግድ ባለቤት ትሆናላችሁ፡፡ ስኬታማ የንግድ ቁልፍ ማግኘት ከፈለጋችሁ ሁልጊዜም ሠራተኞቻችሁን ማበረታታት እና...
የሌሎችን አመለካከት መረዳት መቻል ለስኬታማ መንገድ ምን ያህል አስፈላጊ ነው? ስኬታማ ለመሆን የሰዎችን ችሎታ በዋናነት ማግኘት ይኖርብናነል፡፡ ከሠዎች ጋር ስኬታማ ግንኙነትን ለመፍጠር የእነሱን እይታ መመልከት መቻል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡- 1ኛ የሌሎችን አመለካከት መቀበል ከራሳችን አመለካከት ባሻገር የሌሎችን ብቃት መጋራት ነው፡፡ 2ኛ የሠዎችን አመለካከት መቀበል ርህራሄን እንድናገናዝብ እና ግንኙነትን እንድናጠነክር ይረዳናል፡፡ እነዚህ 2 ሀሳቦች ላይ ስናተኩር ከሠዎች ዘንድ የአክብሮት መስተጋብር፣ስኬት እና በአንድነት ዋስትናን እናገኛለን፡፡ የሠዎችን አመለካከት ለመቀበል የሚረዱ ቀላል መንገዶችን እንመልከት፤ 1. ስለሌሎች ማሰብ በሌሎች ሠዎች ህይወት ውስጥ ስንገባ...
የሀላፊነት ቦታ ላይ ስትሆኑ አብረዋችሁ ከሚሰሩት ሠዎች አክብሮት ማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ አክብሮት ስጦታ አይደለም፤ምንግዜም የሠው ልጅ መከበርን ይፈልጋል፡፡ የስራ ባልደረቦቻችሁ በስራ ገበታ ላይ የማክበር ልምድ ይኖራቸው ይሆናል የእናንተም መረጃ ወይም ችሎታ ስራውን ለማስፈጸም ይጠቅማል ከዚህም ባለፈ መልኩ ግን አክብሮት ያስፈልጋል፡፡ ከሠዎች አክብሮትን ማግኘት ከቻላቹ በቀላል መንገድ ስኬታማ መሆን ትችላላችሁ! ይህንንም አክብሮት ለማግኘት የሚረዳ መላ እናካፍላችሁ፡፡ መልካም ሁኑ በቀን ውስጥ ለምታገኙዋቸው ሠዎች መልካም ጸባይን አሳዩ፡፡ ከቤተሰቦቻችሁ ጀምራቹ እስከ ስራ ባልደረቦቻችሁ እና በመዝናኛ ቦታም ላይ ላሉ ሠዎች ጥሩ ጸባይ ይኑራችሁ፡፡ ለሠዎች መልካም...